שמחה במה שיש
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ለንባብ ጠቃሚ ምክር፦ ከመጽሐፍ ጋር ጓደኝነት መፍጠር
የምትወዱት ቦታ የትኛው ነው? ቤት ውስጥ ነው? ወደ እርሱ ቅርብ ነው? ወይስ ከእርሱ የራቀ ሊሆን ይችላል? እርስ በርሳችሁ መጋራት ትችላላችሁ። ልዩ ቦታችሁና ስለእርሱ የምትወዱት፣ በዓይኖቻችሁ ውስጥ ልዩ የሚያደርገው ምን እንደሆነ።
ጣቢያው
ቆንጆ ቦታ
በሁሉም ቦታ ጥሩ ነገሮችን ማግኘት ይችላሉ። በሁሉም ቦታ የሚገኝ ጸጋ አለ። በእያንዳንዱ የጨዋታው ዙር ከተሳታፊዎች አንዱ በሩቅም ይሁን በቅርብ በእስራኤልም ሆነ በውጪ የሚገኝ ቦታን ይመርጣል፦ እውነተኛም ይሁን ምናባዊ። ሌሎቹ ተሳታፊዎች ስለቦታው ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ። በእነርሱም እርዳታ የተመረጠው ቦታ ለምን ድንቅ ቦታ እንደሆነ ለይተው ያውቃሉ።
ጣቢያው
በአካባቢያችን ውስጥ
ከቤትዎ አጠገብ ምን እየሆነ ነው? ለአጭር ጊዜ ቃኙና በአቅራቢያው ላለው አካባቢ እንዴት አስተዋፅዖ ማድረግ እንደሚችሉ ለማወቅ ይሞክሩ። ወረቀቶችን መሰብሰብና ወደ ገንዳ ማጠራቀሚያ ውስጥ መጣል፣ በአውቶቡስ ማቆሚያ ለሚጠብቁ ሰዎች መጠጥ መስጠት ወይም ከጎረቤቶችዎ ጋር የመንገድ ቤተ መጻህፍት ማደራጀት ይችላሉ።
ጣቢያው
ጣቢያው
ለቤተሰባዊ ንባብ ጠቃሚ ምክር
ታዳጊ ሕጻናት “በስዕላዊ መግለጫዎች ውስጥ ያነባሉ”። ስዕላዊ መግለጫዎችን መመልከት ለዝርዝሮች ትኩረት እንዲሰጡና ለሥነ ጥበብ እንዲጋለጡ ያስተምራቸዋል። ከስዕላዊ መግለጫው ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን አልፎ አልፎ መጠየቅ ትችላላችሁ፤ ለምሳሌ፦ ዝንቡ የት አለ? እስስቷ ምን እያደረገች ነው?
እንዴት መወሰን እንዳለባት የማታውቀው እስስት
በቀለማት ማንበብ
በሚያነቡበት ጊዜ በቃላቱና በስዕሉ ላይ የሚታየውን ዋናውን ቀለም ለታዳጊ ህፃናቱ ማመልከት ይችላሉ። ታዳጊው ሕጻን የቀለም ስም ገና ባያውቅም እንኳ በቀለማት ያሸበረቁ ስዕላዊ መግለጫዎችን በመመልከት ይደሰታል።
እንዴት መወሰን እንዳለባት የማታውቀው እስስት
ፈጠራ - ቀለማትን የምትቀያይር እስስት
ቀለማትን የምትቀያይር እስስት ይፈልጋሉ? – ኮዱን ስካን ያድርጉና የእስስቷን ሥዕል በተንሸራታች ላይ ፕሪንት በማድረግ እንዴት ባለ ቀለም ሊንጠባጠብና አልፎ ተርፎም ሊካተት እንደሚችል ይወቁ።
እንዴት መወሰን እንዳለባት የማታውቀው እስስት
ነገሮች በቀለማት መሰረት
ቀይ ኳስ አላችሁ? በቤታችሁ ውስጥስ ቀይ ሌላ ምን አለ? – አንድን ቀለም ማስታወቅና በተመረጠው ቀለም ውስጥ እቃዎችን ለመሰብሰብ አንድ ላይ መውጣት ትችላላችሁ፦ ዝኩኒ፣ የተከተፈ ተክልና ሌላ ምን አረንጓዴ ነገር ማግኘት ትችላላችሁ?
እንዴት መወሰን እንዳለባት የማታውቀው እስስት
ጨዋታ - እኔ እንደ ማን ነኝ?
“በአራቱም እግሮቼ እየተሳበኩ ቀለሜን እቀያይራለሁ እንደ… እስስት!” በእያንዳንዱ ዙር እንስሳ ላይ ይወሰናል፤ ወላጆች ያሳዩና ታዳጊው ሕጻን ይቀላቀላል፦ “እኛ አንበሶች ነን – ኑ እናግሳ!” “እኛ ቡችላዎች ነን – ኑ እንጩኽና ጅራታችንንም እናወዛውዝ!”
እንዴት መወሰን እንዳለባት የማታውቀው እስስት
እንዴት መወሰን እንዳለባት የማታውቀው እስስት
ውይይት - ይህ በጣም ጥሩና በነፃ ነው
የሚያስደስቱዎና በነጻ የተሰጡዎ ነገሮች የትኞቹ ናቸው? – ሊቁ በነጻ የተሰጡን በዓለማችን ውስጥ ያሉትን መልካም ነገሮች የሚያቀርብበትን ምስል ማየትና እርስ በእርስ መጋራት ይችላሉ – እርስዎም ይደሰቱባቸዋል? ሌሎችስ የትኞቹ ነፃ ክፍያዎች ለእርስዎ ተወዳጆች ናቸው?
ደስታው የሁላችንም ነው
ደስታው የሁላችንም ነው
ስዕላዊ መግለጫዎች - ሴትና ወንድ ልጅ
በመጽሐፉ ውስጥ በተቀመጡት ስዕላዊ መግለጫዎች ላይ በብዛት አንዲት ልጃገረድና አንድ ወንድ ልጅ ይታያሉ። በመጽሃፉ ገፆች መካከል በመፈለግ አንድ ላይ ማሰብ ይችላሉ – ስዕላዊ መግለጫዎቹ ውስጥ ለመጨመር ለምን ሰዓሊዋ የመረጠች ይመስልዎታል?
ደስታው የሁላችንም ነው
ሐላና ጥሩ ሽታ
ሐላን ማዘጋጀት ይፈልጋሉ? – በመጽሐፉ መጨረሻ ላይ እርስዎን የሚጠብቅ የምግብ አዘገጃጀት መመሪያ አለ። መልካም ምግብ ይሁንልዎ፤ ቤቱን በሚሞላው ጥሩ መዓዛ ይደሰቱ።
ደስታው የሁላችንም ነው
ደስታው የሁላችንም ነው
ውይይት - መምረጥና ማዋል
ስለ ሲሪልና ጦብያ ምርጫ መወያየት ተገቢ ነው- በእርስዎ አስተያየት ለምን ሁሉንም ወርቅ ላለመጠቀም የመረጡ ይመስልዎታል? አስገርሞዎታል? በእርስዎ አስተያየት ለምን ወርቁን በትምህርት ላይ ለማዋል መረጡ?
ሰባቱ መልካም ዓመታት
ስዕላዊ መግለጫዎች– ፍየሏ የት አለች?
ፍየሏ በሙሉ ታሪኩ ውስጥ ከሲሪልና ጦብያ ጋር አብራ ትሄዳለች። በመጽሐፉ ስዕላዊ መግለጫዎች ውስጥ ፍየሏን መፈለግ ይችላሉ፦ ምን እየሰራች ነው? ከቤተሰብ ጋር ያላት ግንኙነት ምን ይመስላል? ከፍየሏ እይታ አንጻር ታሪኩን ለመናገር ይሞክሩ – በመጽሃፉ ውስጥ ምን ይገጥማታል?
ሰባቱ መልካም ዓመታት
ጨዋታ– ሃብቱን መፈለግ
ለቤተሰብ አባላት መስጠት የሚፈልጓቸውን ትንንሽ ስጦታዎች ይሰብስቡ፦ ስዕል፣ ቡራኬ ወይም እቃ። በተራው መሰረት ከቤቱ አባላት አንዱ የራሱን ስጦታ ይደብቃል። ሌሎች የቤተሰቡ አባላትም ሀብቱን በምልክቶች ይፈልጉታል፡- “ቅርብ-ሩቅ”፣ “ትኩስ-ቀዝቃዛ” ወይም በቤቱ ዙሪያ የተበታተኑ ቀስቶች።
ሰባቱ መልካም ዓመታት