כִּשּׁוּרֵי חַיִּים
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ለቤተሰባዊ ንባብ ጠቃሚ ምክር
ታዳጊ ሕጻናት የታሪኩ አካል መሆንን ይወዳሉ፦ በመጽሐፉ ውስጥ ያሉትን ቃላትና ድምጾች መድገም ወይም የመጽሐፉን ጀግኖች ድርጊት መተወን። በዚህ መንገድ ታሪኩን ይለያሉ፣ ስሜታዊ የሆነው ዓለማቸውን ያበለጽጋሉ፤ ቃላትንና ጽንሰ-ሐሳቦቻቸውን ያገኛሉ። ስለዚህ የጋራ ንባብ ላይ ጥሩምባን ይዞ “መንፋት”፣ ከበሮውን በእጆቻችሁ “መምታት” እና የሕብረት መዝሙሮች ላይ “መምራት” ይገባል።
ሙዚቃ
ውይይት
ጊሊ ለእርሷ የሚስማማ ሚና አግንታ ኦርኬስትራውን ትመራለች። እርሱን ተከትሎ በቤት ውስጥ ስለ ታዳጊ ሕጻናት ሚናዎች መወያየት ይችላሉ- ምን ያውቃሉና ምን ማድረግ ይፈልጋሉ – መጫወቻዎችን መሰብሰብ? ወለል መጥረግ? ለምግብ ጠረጴዛ ለማዘጋጀት መርዳት?
ሙዚቃ
ሙዚቃ
አብሮ መጫዎት
ማንኛውም ነገር ማለት ይቻላል የሙዚቃ መሳሪያ ሊሆን ይችላል፦ ወደ ዘፈኑ ዜማ እጆቻችሁን በአንድ ላይ ማጨብጨብ ወይም ያገኙትን የሙዚቃ መሳሪያዎች፣ ማራካሾችና መሳሪያዎች መሰብሰብ ይችላሉ። ማንኪያ ያለው ድስት ከበሮ ሊሆን ይችላል፤ ጥቅል ወረቀት እንደ ጥሩምባ ሊያገለግል ይችላል። እንዲሁም የተለያዩ ቁሳቁሶችን በመምታት መሞከርና መፈተን ይችላሉ፦ በእንጨት ሲመታ ምን ዓይነት ድምፆችን ያወጣል? በወለል ንጣፍ ላይስ? በብረት ላይስ? የሚወዱት ዘፈን ላይ ይወስኑና አንድ ላይ መጫወት ይችላሉ።
ሙዚቃ
ኦርኬስትራን መምራት
ማን ነው የሚመራው ማን ነች የምትመራው? – የሚወዱትን ሙዚቃ አንድ ላይ ሲያዳምጡ ትንሽ ዱላ በመያዝ ተጫዋቾቹን “መምራት” ይችላሉ። የሙዚቃው ድምጾች ላይ መደነስና የተለያዩ መሳሪያዎች ላይ መተወን፤ አልፎ አልፎም ሚናዎችን መቀያየር ይችላሉ።
ሙዚቃ
ውይይት - በጋራና በተናጠል
ጋሊና ጋያ ነገሮችን አንድ ላይ ማድረግ ይወዳሉ፤ ግን ደግሞ በተናጠል፦ መወያየትና ማወቅ ትችላላችሁ፦ ታዳጊ ሕጻናት ከወንድም፣ ከሕብረተሰቡ ወይም ከእናንተው ከወላጆች ጋር ምን ማድረግ ይወዳሉ? ብቻቸውንስ ምን ማድረግ ይወዳሉ?
ጋሊና ጋያ
ጋሊና ጋያ ሊጎበኙ ይመጣሉ
ከጋሊና ጋያ ጋር መጫወትና ታሪኩን መተወን ይፈልጋሉ? የQR ኮዱን ስካን ያድርጉና ሁለት የሚያማምሩ ዳክዬዎችን ፕሪንት በማድረግ ቆርጠው በማውጣት ታሪኩን ከእነርሱ ጋር መተወን ይችላሉ…!
ጋሊና ጋያ
בואו אחריי!
משחק תנועה כמו גלי וגאיה, אפשר לצעוד ביחד: תוכלו להכין בבית שביל ולסמן אותו בחבל או בחפצים שונים, וללכת בטור – זה אחר זה ואולי יחד, זה לצד זה. אפשר גם להתחלף, כשכל פעם המוביל קורא: “בואו אחריי!”
או במעון – המחנכת הולכת בכיתת המעון, והפעוטות הולכים אחריה. מדי פעם המחנכת עוצרת ועושה פעולה מסוימת, והפעוטות מחקים אותה: נוגעים באף, קופצים כמו צפרדע, עפים כמו פרפר, נוגעים בחפצים שונים בכיתה ואומרים את השמות שלהם: שולחן, כיסא או ספר.
ጋሊና ጋያ
እንስሳትና ስዕላዊ መግለጫዎች
በግ፣ እንቁራሪት ወይስ ቢራቢሮ? – ምስሎቹን አንድ ላይ ማየትና የተለያዩ እንስሳትን ማግኘት ይገባል። በስዕሉ ውስጥ ያለውን የእንስሳት ድምጽ ማሰማት ወይም እንደርሱ መንቀሳቀስ ይችላሉ፦ እንደ ቢራቢሮ መብረር፣ እንደ ንብ ጥዝዝ ማለት ወይም … ሌላ እንደ ማን?
ጋሊና ጋያ
ተከተለኝ! - የእንቅስቃሴ ጨዋታ
እንደ ጋሊና ጋያ አብረው መራመድ ይችላሉ፦ በቤት ውስጥ መንገድ ማዘጋጀትና በገመድ ወይም በተለያዩ ነገሮች ምልክት በማድረግ በአንድ አምድ ውስጥ መሄድ ይችላሉ – አንዱ ከሌላው በኋላ ወይም ምናልባትም አንድ ላይ ጎን ለጎን። መሪው “ተከተሉኝ!” ብሎ በጠራ ቁጥር መቀያየርም ደግሞ ይቻላል።
ጋሊና ጋያ
ጋሊና ጋያ
አንድ ላይ ማንበብ
ከቤተሰባዊ ንባብ በፊት መጽሐፉን ብቻዎትን ማንበብ አለብዎት። ከመጽሐፉ ጋር ቀደም ብሎ መተዋወቅ በሴትና ወንድ ልጆች ላይ ባለው ፍጥነትና ምት እንዲያነቡዎት ይረዳዎታል። አስደሳች ንባብ!
ተኩላው አይመጣም
ውይይት - መጠበቅ ...
የሆነን ሰው ጠብቀው ያውቃሉ? ተሞክሮዎትን ማጋራትና ስለ መጠበቅዎ እርስ በርስ መነጋገር ይችላሉ። እንዲሁም በሚጠብቁበት ጊዜ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ማሰብና በመጠባበቅ ላይ እያሉ ምን እንዳደረጉ ይናገሩ? በመጨረሻስ ምን ተከሰተ?
ተኩላው አይመጣም
በስራ ላይ ሥዕል መሳል
ጥንቸል እንዴት ይሳላል? ወይም ተኩላ? የQR ኮዱን ስካን በማድረግ የመጽሐፉ ሰዓሊ የሆነው ሮናን ባደል የመጽሐፉን ጀግኖች ሲስል ማየት ይችላሉ።
ተኩላው አይመጣም
ስዕላዊ መግለጫዎችና ፍንጮች
በመጽሐፉ ውስጥ የመጨረሻዎቹን ምስሎች ይመልከቱ። ተኩላው ለጥቂት ሊያመልጠው የነበረውን የልደት ቀን ዝግጅት ፍንጮችን ማግኘት ይችላሉ? ጥንቸሉ የትኞቹን ስጦታዎች ተቀበለ? ተኩላው የሰጠው ልዩ ስጦታስ ምንድነው?
ተኩላው አይመጣም
ጨዋታ - ተኩላ በእንቅስቃሴ ላይ
መጽሐፉን በማሰስ በጨዋታው ውስጥ የሚኖረውን የተራ ቅደም ተከተል ምን እንደሚመስል ትወስናላችሁ። በእያንዳንዱ ተራ ከእናንተ ውስጥ አንዱ በመረጠው ስዕል ይጠቁምና የተኩላውን እንቅስቃሴ ይተውናል፡- በሊፍት መውጣት? በአራት እግር መራመድ? – ቀሪዎቹ ተሳታፊዎች ተኩላው ምን እንደሚያደርግ ለመገመት ይሞክራሉ።
ተኩላው አይመጣም
ተኩላው አይመጣም
ውይይት - ቤታችን
ሁሉም ቤቶች በግድግዳዎችና በጣሪያ፣ በበሮችና በመስኮቶች የተገነቡ ናቸው፦ ስለ ቤትዎ ልዩ ነገር ምንድነው? የእናንተ የሚያደርገው ምኑ ነው? በቤትዎ ውስጥ ስላሉ ነገሮችና ልዩ እቃዎች ብሎም በቤት ውስጥ አብረው ስለሚሰሩ ነገሮች ማውራት ትችላላችሁ።
ቤት እንዴት ይገነባል
ቪዲዮ - ከሳጥኖች የተሠራ ቤት
በቤት ውስጥ ከሳጥኖች ምን ሊሰራ ይችላል? እውነተኛና ምናባዊ የሆነ የቤት ሀሳቦችን ለማግኘት የQR ኮዱን ስካን ያድርጉ።
ቤት እንዴት ይገነባል
ፈጠራ - ቤትን ማን ይሠራል?
ከብርድ ልብሶች፣ ከሣጥኖች፣ ከዱላዎችና ከልብስ መቆንጠጫዎች ለራስዎ ቤት መፍጠር ይችላሉ! ሌላስ ምን ያስፈልጋል? ቦታውንና የስራውን ደረጃ በመወሰን እቃዎችንና አጋዦችን ይሰብስቡና ጉዞ ያድርጉ።
ቤት እንዴት ይገነባል
ጨዋታ - የቤት ውስጥ ታግ
በእያንዳንዱ ዙር ከተሳታፊዎች አንዱ ርዕስን ያስታውቅና ሁሉም ተሳታፊዎች ተባብረው ተገቢውን ዕቃ መፈለግ አለባቸው፦ “ቀይ” ሲባል በቤቱ ውስጥ ያለ ቀይ እቃ ይፈልጉ። በሚቀጥለው ዙር ሌላ ተሳታፊ በፍለጋው ርዕስ ላይ ይወስናል፤ የተቀረው ደግሞ ፍለጋውን ይቀጥላል። ከማስታወቂያው ጋር የሚዛመዱ ነገሮችን መፈለግ ይችላሉ፦ “ትልቅ”፣ “ትንሽ”፣ “ቆንጆ”፣ “አሮጌ”፣ “በቀለም ያሸበረቀ”፣ “አናዳጅ” ወይም “ጎማ”።
ቤት እንዴት ይገነባል
ውይይት - የጠፋው ምንድን ነው?
ለእርስዎ አስፈላጊ የሆነ ነገር ጠፍቶዎት ያውቃል? ምን ተሰማዎትና ምን አደረጉ? ምናልባትም የሌላ ሰው ጠፍቶ አግኝተው ይሆን? መጽሐፉ ሴቶችና ወንዶች ልጆችን እንዲሁም ወላጆችን በመጥፋትና የጠፉት በመገኘት ላይ የልጅነት ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ ይጋብዛል።
ይገኛል!
ቪዲዮ - ጠፍተው የተገኙ እቃዎች ያሉበት ሳጥን
ሻቢና ኦዛም ከ”ደስ የሚል ቢራቢሮ” መርሃ ግብር ላይ የጠፉ እቃዎችን እየመለሱ ነው። ኮዱን ስካን ያድርጉና ይመልከቱ።
ይገኛል!
ጨዋታ - መደበቅና ማግኘት
እያንዳንዱ ተሳታፊ በተራው አንድን ነገር ይመርጥና ይደብቀዋል፤ የተቀሩት ደግሞ መፈለግ አለባቸው። እንደ “ትኩስ-ቀዝቃዛ” ወይም የንብረት ካርታን የመሳሰሉ ፍንጮችን መጠቀም ይችላሉ። አገኙ? ይህ የሚቀጥለው ዙር ጊዜ ነው – መደበቅ፣ መፈለግና ማግኘት።
ይገኛል!
በሥዕላዊ መግለጫዎች ውስጥ መፈለግ
በመጽሐፉ የመጀመሪያ ገጾች ላይ የጠፉ እቃዎች ማስታወቂያዎች ይታያሉ። አብረው አስደሳችና አስገራሚ ማስታወቂያዎችን መፈለግና ለቤተሰብ አባላት ማጋራት ይችላሉ። ከማስታወቂያዎቹ መካከል አንድ የተደበቀ የድርድር ማስታወቂያ አለ – ሊያገኙት ይችላሉ?
ይገኛል!
ይገኛል!
ከትንሽ እስከ ትልቅ
አባዬ ትልቅ ጫማ አለው፣ የእማዬ ጫማ – ትልቅ አይደለም፣ ያኤሊ ትንሽ ጫማ አላት፣ እና የኤሊክ ቤሊክስ? ጥቃቅን ጫማዎች! በቤቱ ውስጥ በሙሉ ጉዞ ይሂዱ፣ ተመሳሳይ አይነት እቃዎችን ይሰብስቡ እና ከትንሽ እስከ ትልቁ ያዘጋጁዋቸው።
ኤሊክ ቤሊክ
አብሮ ማንበብ
እንዲሁም ቤትዎን የሚጎበኙ ትናንሽ ጓደኞች አሉዎት? ምናባዊ ጓደኞች ናቸው፣ ወይም ምናልባት ተወዳጅ አሻንጉሊት? ከታዳጊዎች ጋር ስለ ጉዳዩ ማውራት እና ከትንሽ ጓደኛው ጋር ምን ማድረግ እንደሚወዱ መስማት ጠቃሚ ነው። ታሪኩን ለመቀላቀል እና ለማንበብ ትንሹን ጓደኛውን “ማምጣት” ይችላሉ።
ኤሊክ ቤሊክ
ታሪኩን እንዴት ማንበብ ይቻላል?
ታሪኩ ከወትሮው ትንሽ ረዘም ያለ ነው፣ እናም ፍላጎትን እና የማወቅ ጉጉትን ለመቀስቀስ በተለያዩ ድምጾች መንገር ይመከራል፦ በአባ ድምጽ፣ በያኤሊ ድምጽ እና የተለየ በእማማ እና በኤሊክ ቤሊክ ድምጽ። ስዕላዊ ማብራሪያዎችን አንድ ላይ ማየት እና ታዳጊዎች ዝርዝሮችን በመለየት ላይ እንዲሳተፉ እና “ኤሊክ ቤሊክ (Elik Belik)” የሚሉትን ቃላት እንዲግሙ መጋበዝ ይችላሉ።
ኤሊክ ቤሊክ
የድብብቆሽ ጫወታ
አሻንጉሊቱ የት አለ? ጠረጴዛው ላይ? ምናልባት ከእርሱ ስር? እና ኳሱ የት አለ? የተለያዩ ነገሮችን መደበቅ፣ እነርሱን መፈለግ እና ከዚያ የሚከተሉትን ማለት ይችላሉ፦ “ኳሱ ወንበር ላይ ነው”፣ “ኳሱ በአልጋው ስር ነው”። እንዲሁም ራስዎን መደበቅ እና እርስ በርስ መፈላለግ ትችላላችሁ።
ኤሊክ ቤሊክ
እኛም መርዳት እንችላለን!
ታዳጊዎች በቤት ውስጥ ምን ማድረግ ይችላሉ? ብዙ ነገሮችን! በመመገቢያ ጠረጴዛው ላይ ብርጭቆዎችን ማስቀመጥ፣ በትንሽ መጥረጊያ መጥረግ፣ የቤት እንስሳቱን መመገብ እናም ኩኪዎችን ማቅረብ ይችላሉ። ታዳጊው በቤት ውስጥ እንዴት መርዳት እንደሚችል እና በምን መሳተፍ እንደሚችሉ ወይም ምን እንደሚፈልጉ ማውራት እና ማቅረብ ጥሩ ሀሳብ ነው።
መቅመስ የሚፈልግ ማን ነው? (TIRTZU LIT’OM )
በቤተሰቡ ውስጥ ያለው ማነው?
በታሪኩ ውስጥ ያለው ልጅ ኩኪዎችን ለሌሎች የቤተሰብ አባላት፦ ለአያት፣ አጎት፣ እህት፣ የአጎት ልጅ ይሰጣል። እና የእርስዎ ቤተሰብ አባላት እነማን ናቸው? ስለቤተሰብ አባላት መንገር፣ ስሞቻቸውን እና የያዙትን ሚናዎች መናገር ይችላሉ፣ ለምሳሌ፦ “ሴት አያቴ ብራሃ”፣ “አጎት ባሮክ” እና የቤተሰብ ፎቶዎችን መጠቀም ይችላሉ። እና ያሰራጩ–ኩኪዎች ነበሩዎት…
መቅመስ የሚፈልግ ማን ነው? (TIRTZU LIT’OM )
ባንድነት አንዳንድ ቀላል ያለ ምግብና መጠጥ እናዘጋጅ!
እንደ ቸኮሌት ኳሶች፣ የፍራፍሬ ሳህን ወይም የተቆረጠ ኪያር የመሳሰሉ ምግቦችን አብረው ማዘጋጀት ይችላሉ። የጨዋታ ሊጥ በመጠቀም “የማስመሰል” ምግቦችን ማዘጋጀት እና በቤት ውስጥ ላሉ አሻንጉሊቶች ማቅረብ ይችላሉ።
መቅመስ የሚፈልግ ማን ነው? (TIRTZU LIT’OM )
ጨዋታ፦ አያቴ ኩኪዎች ነበሯት…
“ሴት አያቴ ገንፎ ሰሩ (Grandma made porridge)” የሚለውን ጨዋታ ያውቃሉ? “ልጁ ኩኪዎች ነበረው (The child had cookies)” በተመሳሳይ መንገድ መጫወት ይቻላል፣ ህፃኑ እጇን ወይም እጁን ከፍቶ ወላጁ መቁጠር ይጀምራል፦ “ትንሹ ወንድ ልጅ/ልጃገረዷ ኩኪዎች ነበራት እና አንዱን ለሴት አያቴ (አውራ ጣት በመያዝ)፣ እና አንዱን ለአጎቴ (ጠቋሚ ጣትን በመያዝ) ወዘተ ሰጠ/ች። እና ስለዚህ አንድን የቤተሰብ አባል ለእያንዳንዱ ሰው በመመደብ ጣቶቹን ይቆጥራሉ። የመጨረሻውን ኩኪ ለማን ይሰጣሉ?
መቅመስ የሚፈልግ ማን ነው? (TIRTZU LIT’OM )
መቅመስ የሚፈልግ ማን ነው? (TIRTZU LIT’OM )