דילוג לתוכן המרכזי בעמוד

ኮተንቡታን

በ: ቬሬድ ለባር ምሳሌዎች: ኪኔሬት

ልጆቹ ይሳለቁበታል፤ አባት ይፈራል፤ አያት ትጠራጠራለች። ትንሿ ኤፍራት ግን በእምነት ተሞልታለች። የውጪ ድምፆች በራስ የመተማመን ስሜቷን እንዲያናውጡ አትፈቅድም። ያገኘችውን ትንሽ ጫጩትም ክንፏን ዘርግቶ ለመብረር እስኪችል ድረስ መንከባከቧን ትቀጥላለች። ታላቅ ስራ ስለምትሰራ ትንሽ ልጅ ታሪክ።

የእድሜ ክልል: ቅድመ ትምህርት ቤት

“ሁላችንም ደግነት እንፈልጋለን
[ሁላችንም ደግነት እንፈልጋለን፣ ናታን ዛኽ፣ የተባበሩት ኪቡጽ ፖዓሊም ቤተመጻሕፍት]

ኤፍራት እንዲያድግና ክንፉን እንዲዘረጋ ደግነትና የፍቅር እንክብካቤ የሚያስፈልገውን ትንሽ ጫጩት ታገኛለች። በዙሪያዋ ባሉት ምክሮችና ጥርጣሬዎች ሁሉ ትንሹን ጫጩት በፍቅርና በታማኝነት ታሳድጋለች። ለእርሷም ምስጋና ይድረሳትና በመጨረሻ በእርግጠኝነትና በደስታ የሚበር ወፍ ይሆናል።
ስለ ደግነት፣ ስለሚሰጥ እንክብካቤና ስለ ልጅትና ጫጩት እድገት ታሪክ።”

ማተሚያ ቤት:

כנרת

የስርጭት ዓመት:

תשפ״ד 2023-2024