דילוג לתוכן המרכזי בעמוד

የልብቁልፍ

በ: ኒራ ሃርኤል ምሳሌዎች: ዮሲ አቡላፊያ

አባቱ ዮናታንን ከመዋዕለ ሕፃናት ለመውሰድ ሲመጣ የቤት ቁልፍ እንደጠፋበት አወቀ። አብረውም ለፍለጋ ጉዞ በመውጣት የአባቱን ዓለምና ከሁሉም በላይ አስፈላጊ የሆነውን - ልብን የሚከፍተውን በሚያስደንቅ ሁኔታ ፍለጋ ይጀምራሉ።

የእድሜ ክልል: መዋዕለ ሕጻናት

“””ከዚያም በየቦታው ቁልፎችን እንፈልጋለን አለ ዮናታን። አባቱ ና አለውና ተጓዙ””
አባቶች እቤት በሌሉበት ጊዜ ምን እናደርጋለን? እናቶች በሥራ ላይ ሲሆኑ ምን ዓይነት ፈታኝ ክስተቶችc ያጋጥሟቸዋል? ዮናታንና አባቱ ከቤት ውጭ ራሳቸውን ያገኙና አብረው ቁልፉን ፍለጋ ይሄዳሉ። በጉዞው መጨረሻ ላይ የጠፋውን ቁልፍ እንዲሁም እርስ በርስ ይገናኛሉ። የዮናታን የአባቱን ሕይወት ማየቱ ወደ አባታዊ ዓለም የመግባት ዕድል ስላለው በሁለቱ መካከል ልዩ ቅርርብን ይፈጥራል።

ኒራ ሃርኤል [የተወለደቺው እ.ኤ.አ. በ1936 ነው] ደራሲትና አርታኢዒት ናት። ለህጻናትና ወጣቶች ከስልሳ በላይ መጽሃፎችን የደረሰች ሲሆን በስራዋና “”ዳፍ ዳፍ”” የተሰኘውን ድረ ገጽ ምስረታዋ ብዙ ሽልማቶችን አግኝታለች። ይህም የህፃናትን ስነ-ጽሁፍ ማንበብንና ማወቅን ያበረታታል።

“”ጥሩ የልጆች መፅሃፍ [እርሱ] የሚባለው በሚቀጥለው ቀን የሚያስቡት ዓይነት ሲሆን ነው። አንባቢው ከዚህ በፊት ያልተሰማውን እንዲሰማው ያደርጋል”” [ኒራ ሃርኤል ከግሎብስ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ፣ መጋቢት 2006]

ዮሲ አቡላፊያ (የተወለደው እ.ኤ.አ. በ1946 ነው) ሠዓሊ፣ ካርቱኒስት፣ አኒሜተርና የሕፃናት መጽሐፍት ደራሲ ነው። በስራዎቹ ብዙ ሽልማቶችን አሸንፏል። አቡላፊያ አብዛኞቹን የሜኢር ሻሌቭ መጻህፍትን ምስሎች የሳለ ነው። የእርሱ ምስሎች ዝርዝር የተሞሉ ግን ቀላሎች፣ ፈገግታ የተሞሉና ሰውንና ተፈጥሮን የሚወዱ ናቸው።”

ታሪኩን ተከትሎ የሚመጣ ቪዲዮ

ማተሚያ ቤት:

זברה

የስርጭት ዓመት:

תשפ״ד 2023-2024