דילוג לתוכן המרכזי בעמוד

ምንዓይነትእድልነው!

በ: ሎረንስ ሺመል ምሳሌዎች: ጆን ካሚሎ ሜሮጋ

ጊል የራሱ የላብራዶር ውሻ አለው። ወንድሙ ግን የቤት እንስሳ የለውም። ጊል በጨለማ ውስጥ ማንበብ ይችላል። ወንድሙ ግን ብርሃኑ ሲጠፋ ቆም አለበት። ሆኖም ግን ምንም እንኳን ልዩነታቸው ቢኖርም የጊል ወንድም በእርሱ በጣም ይኮራል። የተለያየ የወንድማማቾች ሕይወት እንዴት እንደሚመስል የሚገልጽ የዋህና ልብ የሚነካ ታሪክ ሳታዩ እንኳን ማየት የምትችሉትን የሚገልጽ።

የእድሜ ክልል: አንደኛ ክፍል

“ቦዔዝ ራሱን እንደ እድለኛ አድርጎ ይቆጥራል። ለወንድሙ ለሃጋይ ምስጋና ይግባውና በቤቱ ውስጥ ውሻ አለው። ወንድሙም እንዴት እንደሚተርክ የሚያውቅባቸውን አስደሳች ታሪኮች ማዳመጥ ያስደስተዋል። ነገር ግን… በእውነት ማየት የተሳነውን ወንድም ታሳቢ ለማድረግ በመገደድ ውስጥ ሆኖ እድለኛ መሆን ይቻላል? ማየት የተሳነው ሰውስ ራሱ እድለኛ መሆን ይችላል? መጽሐፉን ማንበብ የአንድን ዓይነ ስውር ወንድም ያለው ልጅ ዓለም በጥሩ ዓይን የሚያይበትን አዎንታዊ የሆነ እይታን ጨምሮ በሕይወት የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች ያሳያል።

ሰው የሚሄድባትን ቀጥተኛዋ መንገድ የትኛዋ እንደሆነች ውጡና ተመልከቱ። ራቢ ኤሊዔዜር እንዲህ ይላል፦ መልካም የሆነች ዓይን።
(ሚሽና የአባቶች ምዕራፍ 2 9)”

ታሪኩን ተከትሎ የሚመጣ ቪዲዮ

סליחה על השאלה - ילדים עיוורים עונים על שאלות מביכות שהתביישתם לשאול. באדיבות כאן חינוכית

ማተሚያ ቤት:

עוץ

የስርጭት ዓመት:

תשפ״ד 2023-2024