עידוד קריאה
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
እንጀምር!
አንድን ድርጊት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያደርጉት ጥሩ ስሜት ይኖራል – ማንበብ፣ መጻፍ፣ ሌላስ? – ከልጆቻችሁ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረጋችሁትን ወይም የተማራችሁትን ድርጊት ትዝታ ማምጣት ትችላላችሁ፦ ኳሱን ወደ ጎል መምታት፣ ብስክሌት መንዳት፣ መዋኘት ወይም እንቆቅልሽ መፍታት። ሌላስ ምን?
ማንበብና መጻፍ
ቃላት በምስሎች
መጽሐፉን በምስሎች ውስጥ ማንበብ ይቻላል፦ በውስጣቸው ቃላትን ፈልጉ፣ ከልጆች ጋር በመሞከር አንብቡ፣ ፊደሎችን እወቁ፣ በሠዓሊዋ የተጨመሩ አስደሳች ዝርዝሮችን አግኙ።
ማንበብና መጻፍ
ቃላት ቃላት
ዓለም በቃላት የተሞላ ነው – ከመጽሐፉ ውስጥ ትርጓሜን በመምረጥ ለእርሱ የቃላት ዝርዝር ማዘጋጀት ትችላላችሁ – አስቂኝ ቃላት፣ የዳንስ ቃላት፣ የተጫዋች ቃላት፣ የሚያብቡ ቃላት። እንደ ቀጭኔ ያሉ ረጃጅም ቃላትና አጫጭር ቃላት። ምናልባትም በጣም የምትወዷቸውን ቃላት ዝርዝር ማዘጋጀት ትፈልጉ ይሆናል።
ማንበብና መጻፍ
ንግግር
አዲስ ችሎታ ያገኛችሁባቸውን ጊዜያት የምታስታውሷቸውን ገጠመኞች እርስ በርሳችሁ ማውራትና ማካፈል አለባችሁ፦ የተጸውዖን ስም መፃፍ፣ የሳላችሁትን ልዩ ሥእልና ሌላስ? የትኞቹን አዳዲስ ችሎታዎች የበለጠ ለማወቅ ትፈልጋላችሁ?
የስጦታው ብዕር
የመጻሕፍት ሥእሎች
“የስጦታው ብዕር” የተሰኘው መጽሐፍ ውስጥ ያሉት ሥእሎች እኛን አንባቢዎችን መጽሐፉና የላው ዓለም ውስጥ “እንድንገባ” ይጋብዙናል፦ ላውን የሚሸኘው እንስሳ የትኛው ነው? በምሳሌዎቹ ውስጥ የትኞቹ እንስሳት ይታያሉ? በታሪኩ ውስጥ ከልጆችና ከእንስሳት ዓለም የትኞቹ ዝርዝሮች ተወስደዋል? ምናልባትም የላው ሥዕሎችን በመከተል የራሳችሁን ሥዕል መሳል ትፈልጉ ይሆን?
የስጦታው ብዕር
የብዕር ጊዜ
በእናንተው ብዕር ውስጥ ምን ድንቅ ነገሮች ይጠብቋችኋል? የማስታወሻ ደብተርን ለሥዕሎች መሳያ፣ ለቃላት መቅጃና ተወዳጅ ቃላትን መጻፊያ ማዋል ይቻላል። ይህም እያንዳንዳችሁ ሥዕሎችንና ቃላትን ልትጨምሩ የምትችሉበት የቤተሰብ ማስታወሻ ደብተር ሊሆን ይችላል።
የስጦታው ብዕር
የጋራ ሥዕል
በብዕርዎ ውስጥ የትኛው ዓለም ተደብቋል? በብዕርና ወረቀት እገዛ ማወቅ ትችላላችሁ! ከቤተሰቡ አንድ ሰው በሥዕል ይጀምራል፤ ሁሉም እያንዳንዱ በተራው ለሥዕሉ እቃ ይጨምራል- መስመር፣ ክብ፣ ምስል ወይም የሆነ ነገር- እናም ከአንድ ብዕር የወጣ በጋራ የተሳለ ወጥ ሥዕልን ይፈጥራሉ!
የስጦታው ብዕር
פינטרסט
פינטרסט- ሥዕሎችና የፈጠራ ስራዎች “የስጦታው ብዕር” በተሰኘው መጽሃፍ ገጽ ላይ, በፒጃማ ቤተ-መጽሐፍት ፒንተረስት ላይ ይገኛል።
የስጦታው ብዕር