חורף וגשם
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
መነጋገር - ማን ሊያግዝ ይችላል?
ሁሉም ሰው ሌሎችን ታዳጊ ሕጻናትን እንኳን ሳይቀር ሊያግዝ ይችላል። ታዳጊ ሕጻናቱን ሌሎችን በምን እንደሚያግዙ መጠየቅ ወይም በሚከሰትበት ጊዜ እንደሚረዷቸው መንገር ይችላሉ፦ “ጠረጴዛውን ለማዘጋጀት እንደረዳኸኝ አስታውስ?”፣ “መጫዎቻዎቹን ለማዘጋጀት እንዴት እንደረዳሽኝ ተመልከቺ!”
ኖኒ እና እናት ከመዋዕለ ህጻናት በመጓዝ ላይ ናቸው።
ታሪኩን ማዳመጥ
“ኖኒና እናቱ” የሚለውን ታሪክ ማዳመጥ ይፈልጋሉ? – የQR ኮዱን ስካን ያድርጉና የታሪኩ የድምጽ ቅጂ ላይ ይደርሳሉ። በሚያሽከረክሩበት ጊዜ፣ በሚጫወቱበት ወይም አብረው ተቀምጠው መጽሐፍ በሚያገላብጡበት ጊዜ ማዳመጥ ይችላሉ።
ኖኒ እና እናት ከመዋዕለ ህጻናት በመጓዝ ላይ ናቸው።
ታሪኩ በምስል
ስዕሎቹ የታሪኩ አካል ሲሆኑ በእነርሱ አማካኝነት ታዳጊ ሕጻናቱ የታሪኩን ሂደትና ዝርዝሮቹን ያውቃሉ፤ ያስታውሳሉም። ስዕላዊ መግለጫዎቹን አንድ ላይ በማየት ኖኒ ለእናቱ የሰጣትን ዕቃዎች መፈለግ ይቻላል። ‘ቦርሳ የተሳለበት ቦታ የት ነው?’ እና ‘የኮት ምስል የት አለ?’
ኖኒ እና እናት ከመዋዕለ ህጻናት በመጓዝ ላይ ናቸው።
ጨዋታ - የእቃዎች ግንብ
በእናት ላይ በተቆለሉ ነገሮች በመጠቀም በተራ የእቃዎችን ግንብ መገንባት ይችላሉ፦ በጥንቃቄ አንዱን በሌላው ላይ በማድረግ ኩቦችን፣ መጫወቻዎችን፣ ኮፍያዎችን፣ ቦርሳዎችንና ማከል የሚፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ማስቀመጥ ይችላሉ።
ኖኒ እና እናት ከመዋዕለ ህጻናት በመጓዝ ላይ ናቸው።
ኖኒ እና እናት ከመዋዕለ ህጻናት በመጓዝ ላይ ናቸው።
ውይይት - ሸምበቆ ወይስ ዝግባ?
በሕይወት ውስጥ ስለ መቀያየርና መቋቋም ማውራት እንችላለን። እንደ ዝግባ ባለንበት ከአቋማችን ለመንቀሳቀስ ዝግጁ ባልሆንባቸው ሁኔታዎችና ተለዋዋጭ በሆንባቸው ባህርያችንን ወይም አስተሳሰባችንንም በምንቀይርባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ከዕለት ተዕለት ሕይወት ምሳሌዎችን ማጋራት ጠቃሚ ነው – ፍላጎቶቻችን እንደጠበቅናቸው መሟላት ሳይችሉ ሲቀር ምን ይከሰታል?
ሸምበቆውና ዝግባው
ታሪክ ይስሙ
የመጽሐፉ ማጀቢያ የQR ኮዱን ስካን በማድረግ ይጠብቅዎታል በማንኛውም ጊዜ ዘና ማለትና ታሪኩን አብረው ማዳመጥ ይችላሉ። እንዲሁም ለአዲስ ገቢ ቤተሰቦች ተስማሚ ነው።
ሸምበቆውና ዝግባው
ሰውነትን የማቀያየር መልመጃ
ጉልበቶችዎ እርስ በእርሳቸው እንዲተያዩ ሆነው መቀመጥ። ወደ ውስጥ መተንፈስና እጆቻችሁ ከላይ እስኪደርሱ ድረስ ወደ ሰውነታችሁ ጎን ማንሳት። ከዚያም እጆችዎን ወደ ፊት በሚያወርዱበት ጊዜ አየሩን ወደ ውጪ ማስወጣት። በእያንዳንዱ ጊዜ ትንሽ ልምምድ እያደረጉና ተጨማሪ ልምምዶችን ማድረግ ይኖርብዎታል። ለጤና ያድርግልዎት!
ሸምበቆውና ዝግባው
የሸምበቆ-ዝግባ ጨዋታ
የሸምበቆ ተቃራኒው ምንድን ነው? – ዝግባ! የሙቀትስ ተቃራኒው ምንድነው? – ቀዝቃዛ! የአሮጌስ ተቃራኒ? ተለዋዋጭ? የተረጋጋ? ኮምጣጣ? ሕፃን? – እያንዳንዱ ተሳታፊ በተራው አንድ ቃል ይናገራል፤ የተቀሩት ደግሞ የተቃራኒውን ቃል ማግኘት አለባቸው። የ… ተቃራኒስ ተቃራኒው ምንድን ነው?
ሸምበቆውና ዝግባው
ሸምበቆውና ዝግባው
ውይይት - በምናብ አብሮ ማሰብ
ወንድና ሴት ልጆች የምናብ ጨዋታዎችን መጫወት ይወዳሉ። አዋቂ መስሎ መኪና ለ”መንዳት” መሞከር፣ ከጭቃ “ኬክ” መስራትና ከምናባዊ ጓደኛቸው ጋር መጫወት ያስደስታቸዋል። እንደ አሻንጉሊት፣ ድስት ወይም የመጫዎቻ መኪና ባሉ ነገሮች ዙሪያ ከልጆች ጋር አብሮ መጫወትና መጠየቅ ይቻላል – ወደየት እየሄድን ነው? አብረን ምን እናብስል? አሻንጉሊቱ ምን ይላል?
ምስል
ፈጠራ - በውሃ ውስጥ ያለ ነጸብራቅ
ነጸብራቅ መስራት ይፈልጋሉ? በኩሬው ውስጥ እንደሚያዩት? – የኪው አር ኮዱን ስካን በማድረግ ለቀላል ፈጠራ መነሳሻን ማግኘት ይችላሉ።
ምስል
ጨዋታ - ራሱን ቁጭ
ሮን በኩሬው ውስጥ አንድ ምስል ተመለከተ፤ ነገር ግን በእውነቱ በውሃው ውስጥ የሚንፀባረቀው የራሱ ምስል ነው። የ”መስታወት” ጨዋታን መጫወት ይችላሉ። ሁለት የቤተሰብ አባላት እርስ በእርሳቸው ፊት ለፊት ይቆማሉ፦ በተራው መሰረት አንዱ “የፊት ቅርጽ” እየሰራ ጭንቅላቱን ወይም እግሩን ያንቀሳቅሳል፤ ሌላኛው ደግሞ እርሱን ለመምሰል ይሞክራል።
ምስል
እንቅስቃሴ - በኩሬ ውስጥ መዝለል
ከውጪ በኩል ኩሬዎች አሉ? – ቡትስ ጫማዎችን በማድረግ በደንብ ለብሶ ወደ ውጪ መውጣትና በኩሬ ውስጥ መዝለል ይችላሉ። መውጣት ተገቢ ካልሆነስ? – ከገመድ ወይም ከወረቀት “ኩሬ” መስራትና የፈለጉትን ያህል ወደ ውስጥና ወደ ውጪ መዝለል ይችላሉ…
ምስል
פינטרסט
עוד יצירות והשראה מחכים לכם בתיקיית הספר בפינטרסט של ספריית פיג’מה!
ምስል