בעלי חיים וטבע
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ለንባብ ጠቃሚ ምክር፦ ከመጽሐፍ ጋር ጓደኝነት መፍጠር
ከትንሽነታቸው ጀምሮ መጻህፍትን ማንበብ ለጨቅላ ሕፃናት እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል። በዝግታና ቀስ በቀስ ማንበብ መጀመር ይመከራል። መጀመሪያ ላይ ታዳጊው በራሱ መንገድ ከመጽሐፉ ጋር መገናኘት ይችላል፦ ይዳስሰዋል፣ ይከፍተዋል ይዘጋዋል፣ ምስሎችን ይመለከትና ለማወቅ ይጓጓል። ከዚያ ማንበብ ይችላሉ፦ በየቀኑ ትንሽ፣ በትዕግስትና በእርጋታ ማንበብ። አንድ ገጽ ብቻ ማንበብ የሚመርጡ ታዳጊዎች አሉ፣ ማዎቅ፣ ማለማመድና እነሆ – መጽሐፉ ጓደኛ ሆኗል!
አንድ ትንሽ ልጅ ወደ መዋእለ ህጻናት ሄደ
በመንገድ ላይ ምን ይከሰታል
ትኩረት የምንሰጥ ከሆነ አስደሳች ግኝቶችን ማግኘት ይቻላል። በመንገድ ላይ ስለሚያዩት ነገር፣ በእግር ወይም መኪና ሲነዱ ማውራት ይችላሉ። “ቀይ መኪና ይኸውና!” “ደመና አያለሁ አንተስ ምን ታያለህ?” እንዲሁም ከታዳጊዎች ጋር መካፈልና ልምዶችን መለዋወጥ ይችላሉ፦ “ወደ ሥራ መንገድ ላይ አንዲት ሴት ከውሻ ጋር ስትራመድ አየሁ ዛሬ ወደ ሕጻናት ማቆያው ወይም ከእርሱ ስትመለስ ምን አየህ?”
አንድ ትንሽ ልጅ ወደ መዋእለ ህጻናት ሄደ
የጠዋት ሥነ ሥርዓት
በመጽሃፉ ውስጥ እንዳለው ልጅ, ታዳጊዎችም እንዲሁ መደበኛ አሰራርን የሚፈጥሩ የአምልኮ ሥርዓቶች ይወዳሉ, የሚያረጋጉ እና ቀኑን በጥሩ ስሜት እና ደስታ እንዲጀምሩ ይረዷቸዋል. ጠዋት ላይ የእራስዎን ትንሽ የጠዋት ሥነ ሥርዓት ማካሄድ ይችላሉ – ለምሳሌ, ታዳጊው ለተወዳጅ ቴዲ ድብ እንዲሰናበት ማበረታታት ይችላሉ: “ዱቢ, ቴዲ, ወደ ኪንደርጋርተን እሄዳለሁ, ሰላም!” እና እርስዎ, ወላጆች, በድብ ስም መልስ ይሰጣሉ: “ሰላም, ሰላም እና በረከት! እና የተሳካ መንገድ!”
አንድ ትንሽ ልጅ ወደ መዋእለ ህጻናት ሄደ
ከእንስሳት ጋር መገናኘት
በመጽሐፉ ውስጥ ብዙ እንስሳት ይታያሉ። አንድ ላይ ሆነው እነርሱን በመመልከት ስማቸውን መጥቀስ፣ የእንስሳትን ድምፅ ማሰማት ወይም እንቅስቃሴያቸውን ማስመሰል ትችላካችሁ። እንደ ዶሮ መጮህ፣ እንደ ጥንቸል መዝለል ወይም እንደ ፈረስ መጋለብና መጮህ ይችላሉ። እንዲሁም በመጨረሻው ገጽ ላይ ያሉትን ምስሎች በመመልከት በእያንዳንዱ ጊዜ ከእንስሳቱ ውስጥ አንዱን በመደበቅ የሚሰማውን ድምጽ በማሰማት ወይም እንቅስቃሴውን በማስመሰል ታዳጊው የትኛው እንስሳ እንደሆነ እንዲገምት መጠየቅ ይችላሉ።
አንድ ትንሽ ልጅ ወደ መዋእለ ህጻናት ሄደ
לקרየቤተሰባዊ ንባብ ምክር וא עם פעוטות
የግጥም መጽሐፍን በሚያነቡበት ጊዜ በአንድ ጊዜ አንድ ግጥም ላይ በማተኮር ብዙ ጊዜ ማንበብ ወይም ዜማ ካለው መዝፈን ይችላሉ። ምስሎችን አንድ ላይ በመመልከት የታዳጊው ወይም የታዳጊዋ ትኩረት የሚሳብበትን ቦታ ማየት ጠቃሚ ነው። ከጊዜ ወደ ጊዜ ከመጽሐፉ ውስጥ ሌላ ግጥም በማጣመር ምን አይነት ምላሾች እንደሚያስነሳ ብሎም አስደሳችና ትኩረት የሚስብ መሆኑን ማየት ይችላሉ።
እኔና ሁሉም ዓይነት እንስሳት
እኛና ሌሎች እንስሳት
በመጽሐፉ ውስጥ የተለያዩ እንስሳትን ያገኛሉ። አንዳንዶቹ ለታዳጊ ህፃናት የተለመዱ ሲሆኑ አንዳንዶቹ አዲስና አስደሳች ናቸው። በአቅራቢያዎ ካለው እንስሳ ጋር ሲገናኙ የታዳጊዎቹን ትኩረት ወደ እንስሳው ልዩ ነገር መምራት ይችላሉ – “ወፉ ምንቃር አለው”፣ “ጉንዳኖቹ በሕብረት ይሄዳሉ” ወይም “ቀንድ አውጣው በጀርባው ላይ ቤት አለው”።
እኔና ሁሉም ዓይነት እንስሳት
በመላው ሰውነት መዝፈን
ዘፈኑን በእንቅስቃሴዎች ማጀብ ይችላሉ። ለምሳሌ፦ “ደስ የሚል ቢራቢሮ ሆይ ወደ እኔ ና” በሚለው ዘፈን ውስጥ ቢራቢሮውን በእንቅስቃሴ “ና” በማለት መጋበዝ ትችላላችሁ። በእጆችዎ መብረርና የታዳጊውን መዳፍ መንካት። በሳቅ ለሚፈነዳ ዝንጀሮስ የሚስማማው እንቅስቃሴ ምን አይነት ይሆን? ወይስ መሰላሉን ለሚወጣው ድብ?
እኔና ሁሉም ዓይነት እንስሳት
እኔና ሁሉም ዓይነት እንስሳት
ለቤተሰባዊ ንባብ ጠቃሚ ምክር
ታዳጊ ሕጻናት “በስዕላዊ መግለጫዎች ውስጥ ያነባሉ”። ስዕላዊ መግለጫዎችን መመልከት ለዝርዝሮች ትኩረት እንዲሰጡና ለሥነ ጥበብ እንዲጋለጡ ያስተምራቸዋል። ከስዕላዊ መግለጫው ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን አልፎ አልፎ መጠየቅ ትችላላችሁ፤ ለምሳሌ፦ ዝንቡ የት አለ? እስስቷ ምን እያደረገች ነው?
እንዴት መወሰን እንዳለባት የማታውቀው እስስት
በቀለማት ማንበብ
በሚያነቡበት ጊዜ በቃላቱና በስዕሉ ላይ የሚታየውን ዋናውን ቀለም ለታዳጊ ህፃናቱ ማመልከት ይችላሉ። ታዳጊው ሕጻን የቀለም ስም ገና ባያውቅም እንኳ በቀለማት ያሸበረቁ ስዕላዊ መግለጫዎችን በመመልከት ይደሰታል።
እንዴት መወሰን እንዳለባት የማታውቀው እስስት
ፈጠራ - ቀለማትን የምትቀያይር እስስት
ቀለማትን የምትቀያይር እስስት ይፈልጋሉ? – ኮዱን ስካን ያድርጉና የእስስቷን ሥዕል በተንሸራታች ላይ ፕሪንት በማድረግ እንዴት ባለ ቀለም ሊንጠባጠብና አልፎ ተርፎም ሊካተት እንደሚችል ይወቁ።
እንዴት መወሰን እንዳለባት የማታውቀው እስስት
ነገሮች በቀለማት መሰረት
ቀይ ኳስ አላችሁ? በቤታችሁ ውስጥስ ቀይ ሌላ ምን አለ? – አንድን ቀለም ማስታወቅና በተመረጠው ቀለም ውስጥ እቃዎችን ለመሰብሰብ አንድ ላይ መውጣት ትችላላችሁ፦ ዝኩኒ፣ የተከተፈ ተክልና ሌላ ምን አረንጓዴ ነገር ማግኘት ትችላላችሁ?
እንዴት መወሰን እንዳለባት የማታውቀው እስስት
ጨዋታ - እኔ እንደ ማን ነኝ?
“በአራቱም እግሮቼ እየተሳበኩ ቀለሜን እቀያይራለሁ እንደ… እስስት!” በእያንዳንዱ ዙር እንስሳ ላይ ይወሰናል፤ ወላጆች ያሳዩና ታዳጊው ሕጻን ይቀላቀላል፦ “እኛ አንበሶች ነን – ኑ እናግሳ!” “እኛ ቡችላዎች ነን – ኑ እንጩኽና ጅራታችንንም እናወዛውዝ!”
እንዴት መወሰን እንዳለባት የማታውቀው እስስት
እንዴት መወሰን እንዳለባት የማታውቀው እስስት
ውይይት - በጋራና በተናጠል
ጋሊና ጋያ ነገሮችን አንድ ላይ ማድረግ ይወዳሉ፤ ግን ደግሞ በተናጠል፦ መወያየትና ማወቅ ትችላላችሁ፦ ታዳጊ ሕጻናት ከወንድም፣ ከሕብረተሰቡ ወይም ከእናንተው ከወላጆች ጋር ምን ማድረግ ይወዳሉ? ብቻቸውንስ ምን ማድረግ ይወዳሉ?
ጋሊና ጋያ
ጋሊና ጋያ ሊጎበኙ ይመጣሉ
ከጋሊና ጋያ ጋር መጫወትና ታሪኩን መተወን ይፈልጋሉ? የQR ኮዱን ስካን ያድርጉና ሁለት የሚያማምሩ ዳክዬዎችን ፕሪንት በማድረግ ቆርጠው በማውጣት ታሪኩን ከእነርሱ ጋር መተወን ይችላሉ…!
ጋሊና ጋያ
בואו אחריי!
משחק תנועה כמו גלי וגאיה, אפשר לצעוד ביחד: תוכלו להכין בבית שביל ולסמן אותו בחבל או בחפצים שונים, וללכת בטור – זה אחר זה ואולי יחד, זה לצד זה. אפשר גם להתחלף, כשכל פעם המוביל קורא: “בואו אחריי!”
או במעון – המחנכת הולכת בכיתת המעון, והפעוטות הולכים אחריה. מדי פעם המחנכת עוצרת ועושה פעולה מסוימת, והפעוטות מחקים אותה: נוגעים באף, קופצים כמו צפרדע, עפים כמו פרפר, נוגעים בחפצים שונים בכיתה ואומרים את השמות שלהם: שולחן, כיסא או ספר.
ጋሊና ጋያ
እንስሳትና ስዕላዊ መግለጫዎች
በግ፣ እንቁራሪት ወይስ ቢራቢሮ? – ምስሎቹን አንድ ላይ ማየትና የተለያዩ እንስሳትን ማግኘት ይገባል። በስዕሉ ውስጥ ያለውን የእንስሳት ድምጽ ማሰማት ወይም እንደርሱ መንቀሳቀስ ይችላሉ፦ እንደ ቢራቢሮ መብረር፣ እንደ ንብ ጥዝዝ ማለት ወይም … ሌላ እንደ ማን?
ጋሊና ጋያ
ተከተለኝ! - የእንቅስቃሴ ጨዋታ
እንደ ጋሊና ጋያ አብረው መራመድ ይችላሉ፦ በቤት ውስጥ መንገድ ማዘጋጀትና በገመድ ወይም በተለያዩ ነገሮች ምልክት በማድረግ በአንድ አምድ ውስጥ መሄድ ይችላሉ – አንዱ ከሌላው በኋላ ወይም ምናልባትም አንድ ላይ ጎን ለጎን። መሪው “ተከተሉኝ!” ብሎ በጠራ ቁጥር መቀያየርም ደግሞ ይቻላል።
ጋሊና ጋያ
ጋሊና ጋያ
መልካም ውይይት
ከንባቡ በኋላ መወያየትና መጠየቅ ይቻላል፡- በእርስዎ አስተያየት የአጎት ስም ለምን ሲምሓ ተባለ? እርሱ ከሚያደርጋቸው ወይም ከሚናገራቸው ነገሮች ምን ምን ፈገግ አስኘዎት?
አጎቴ ሲምሓ
'አጎቴ ሲምሓ'ን ማዳመጥ
ታሪክ መስማት ይፈልጋሉ? – የኪው አር ኮዱን ስካን ካደረጉ ስለ አጎቴ ሲምሓ ያለውን ታሪክ ማዳመጥ ይችላሉ። በፈለጉት ጊዜ በጋራ በመሆን ማዳመጥና ማሰስ ይመከራል።
አጎቴ ሲምሓ
አስደሳች ዘፈኖች
የትኞቹ ዘፈኖች ያስደስቱዎታል? አስደሳች የቤተሰብ አጫዋች ዝርዝር ማዘጋጀትና በጋራ መዝፈን ይችላሉ። እንዲሁም በአስቂኝ ድምፆች መዝፈን ይችላሉ፦ በቀጭን ድምጽ፣ በወፍራም ድምጽ፣ በሹክሹክታና ደስታን የሚያመጡ እንቅስቃሴዎችን በመጨመር።
አጎቴ ሲምሓ
አጎት ግራ ተጋብቷል - ግራ የተጋባ ጨዋታ
እያንዳንዱ ተሳታፊ በተራው አንድ ጥያቄ ይጠይቃል፤ ሌሎች ተሳታፊዎችም “ግራ የተጋባ” መልስ ይፈልጋሉ። ለምሳሌ፡- የምትወደው መጠጥ ምንድነው? ሻይ ከስናፍጭ ማንኪያ ጋር! ዝናብ ሲዘንብ ምን ታደርጋለህ? የፀሐይ መከላከያን መቀባት! ወፎች ምን ዓይነት ድምጾች ያወጣሉ? ወደየት መውጣትና መጎብኘት ይመከራል?
አጎቴ ሲምሓ
አብሮ ማንበብ
ታሪኩን በማንበብ በንቃት እንዲቀላቀሉ ታዳጊዎቹን ማበረታታት ይችላሉ። እነርሱ የግጥም ቃላትን ማጠናቀቅ፣ በፊት ገጽታ እና በትክክለኛ የእጅ ምልክቶች በእንስሳት መካከል የሚደረገውን ውይይት ማጀብ እና በታሪኩ ውስጥ የሚታዩ የእንስሳትን ድምጽ መፍጠር ይችላሉ።
ሰንበት በጫካ ውስጥ
ሰንበትን ወደ መቀበል
ታዳጊዎችን መጠየቅ ይችላሉ፦ በሰንበት ምን ማድረግ ይወዳሉ? ቤተሰቡ ለሰንበት ልዩ ዝግጅቶች ካላቸው፣ እነርሱን ለልጁ መንገር እና ማጋራት ጠቃሚ ነው
ሰንበት በጫካ ውስጥ
እንስሳቶቹ የት አሉ?
መጽሐፉ ንብ፣ ኤሊ፣ ጉንዳን፣ ዶሮ፣ ላም እና ጥንቸል በተለይ ይገልፃል። በመፅሃፉ ውስጥ ባሉት ስዕላዊ ማብራሪያዎች ውስጥ ታዳጊዎች የተለያዩ እንስሳትን እንዲለዩ ጠይቋቸው እናም እያንዳንዱን እንስሳ በልዩ ድምፅ አጅበው ወይም ሌላ የባህሪይ ዝርዝሮችን ይጨምሩበት፦ ንቧ ኸምምም ትላለች፣ ጥንቸሉ ይፈናጠራል፣ ኤሊ በዝግታ ትሳባለች፣ እና ላሟ ትጮኻለች።
ሰንበት በጫካ ውስጥ
እናም አሁን - ኤሊ!
በእጅዎ መዳፍ ኤሊ እንዴት ይሰራል? መዳፉን በቡጢ ይዝጉና በውስጡ አውራ ጣትን ይደብቁ። ኤሊውን ወደ ውጪ ይጥሩ፣ አውራ ጣትን አውጥተው ሰላም በማለትያንቀሳቅሱት። እቤት ውስጥ ከሚገኙ በሁሉም መዳፎች ብዙ ዔሊዎችን መፍጠር ትችላላችሁ እራስዎ ኤሊ መሆን እና በአራት እግሮች ላይ በዝግታ መሄድ ይችላሉ። ደክሞታል ወይ? በ”ቤትዎ” ውስጥ ለማረፍ ወደ ውስጥ ይግቡ።
ሰንበት በጫካ ውስጥ
Pinterest – የእደ-ጥበቦች፣ መዝሙሮች እና ሌሎች ተግባራት “ሰንበት በጫካ ውስጥ በሚለው መጽሐፍ ገጽ ላይ በሲፍሪያት ፒጃማ ውስጥ በ Pinterest ላይ።
ሰንበት በጫካ ውስጥ