אֲנִי וְעַצְמִי
סבלנות
"סבלנות – לא קונים בשום חנות!" מדקלמות גננות ומדקלמים הורים במשך שנים, בניסיון להנחיל מיומנויות התנהגות של המתנה ושל דחיית סיפוקים. כמה שזה קשה! ספרים שעוסקים בקושי לחכות, להתאפק ולהמתין כשצריך, יכולים לסייע בשכלול המיומנות והיכולות להתאזר בסבלנות.
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
መጀመርያ እንዲገባ የሚለው ሃሳብ መልካም ነበር
ታሪኩን በመከተል መወያየት፣ ማጋራትና መጠየቅ ይችላሉ፦ ወረፋ ሲጠብቁ ምን ይሰማዎታል? የእኛ ተራ ከሌሎች የበለጠ አጣዳፊ እንደሆነ ተሰምቶን ያውቃል? አንድ ቡችላ እርሱን ግምት ውስጥ ያስገቡት መሆኑን በምን የሚያውቅ ይመስልዎታል? ኮፊፍና ሌሎች የሚጠባበቁ ሰዎች ተራቸውን ከለቀቁ በኋላ ምን ተሰማቸው? እርስዎን ግምት ውስጥ ስላስገቡ ሰዎች ወይም እርስዎ ሌሎችን ግምት ውስጥ ያስገቡበት ሁኔታ አብረው ለማስታወስ ይሞክሩ።
ተረኛው ማን ነው?
ኮፊፍ፣ ቀጭኔ፣ ዝሆንና አዞ የተራውን ቅደም ተከተል የሚወስን መርህ ለማግኘት ይሞክራሉ። በእነርሱ ተነሳሽነት እያንዳንዱን ጊዜ በተለየ ቅደም ተከተል የሚያስተዳድሩበት ከሁሉም የቤተሰብ አባላት ጋር በመሆን አዝናኝ ጨዋታ መጫወት ይችላሉ። ለምሳሌ፦ በእድሜ ከወጣት እስከ ሽማግሌ ወይም በሸሚዝ ቀለም ከደማቅ እስከ ፈዛዛ ምናልባትም ምን ያህል አይስ ክሬምን እንደሚወዱ ቅደም ተከተልን መስጠት ይችላሉ። የተለያዩ አዝናኝ ባህሪያትን በአንድ ላይ ማምጣትና ማረጋገጥ ይቻላል- አሁን ላይ ማን ነው ቀጣዩ?
ጠብቆ መዝናናት
ኮፊፍ የጥበቃ ጊዜውን ያሳለፈው እንዴት ነው? አብረውት ከሚጠባበቁት ጋር ተነጋግሮ ለወረፋው ቅደም ተከተል ሀሳብ በማቅረብ አዳዲስ ጓደኞችን አፍርቷል። እርስዎም አንድ ላይ ሆነው አንድ ነገር ሲጠብቁ ጊዜዎን እንዲያሳልፉ የሚያግዙ ሀሳቦችን ማምጣት ይችላሉ። በተጠባባቂ ላይ እያሉ ሊዘፍኑት የሚችሉትን አዝናኝ ዘፈን፣ የጣት እንቅስቃሴ ጨዋታና ጊዜውን እንዲያሳልፉ የሚረዳዎትን ሃሳብ መስራት ይችላሉ – መጽሐፍ፣ የስዕል ደብተር፣ እንቆቅልሽ፣ የመከላክል ኳስ። ወይም ወደ አእምሮዎ የሚመጣ ሌላ ማንኛውም አዝናኝ ሀሳብ።
ቀጣዩ ተረኛ
ሃርሞኒካው
ረዥሙመንገድ


