סבלנות
סְּפָרִים
ተወያዩ
ስትወላወሉና ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ሳታውቁ ስትቀሩ ምን ታደርጋላችሁ? ከማን ምክር ለማግኘት ደስ ይላችኋል? ከማን ምክር መቀበል ይከብዳችኋልና ለምን? – አንዳንድ ጊዜ ጥሩ ምክሮች ሳይታሰቡ ይመጣሉ፦ ከልጆቻችሁ ጋር ስለ ጉዳዩ ማውራት ትችላላችሁ። ምክር ያዳመጡትን ጊዜ በማስታወስ ከታላላቅና ወጣት ሰዎች የተማራችሁትን አካፍሉ።
ረዥሙመንገድ
በመንገዱ ስለመደሰት
ለመንገድ ወጥታችሁና ረዥም ሆነ? ምናልባት አሰልቺ? – በጉዞው ወቅት መጫወት ይቻላል፦ በመንገድ ላይ ያሉ ታፔላዎችን መቁጠር፣ የተለመዱ ፊደላትን መለየት፣ የዓመት ወቅቶችን ተከትሎ በአካባቢው ለውጦችን ማግኘት፣ ተወዳጅ ዘፈኖችን መዝፈን፣ እንዲሁም … መንገዱን ማጤንና እስካሁን ድረስ ያላስተዋላችኋቸውን ነገሮች ላይ መደሰት።
ረዥሙመንገድ
ከእያንዳንዱ ሰው ስለመማር
ልጆች አዋቂዎችን ምን ማስተማር ይችላሉ? አዋቂዎችስ ልጆችን ምን ማስተማር ይችላሉ? እውቀታችሁን እርስ በርሳችሁ ማካፈል አለባችሁ፤ አብራችሁም ልትለማመዱት ትችላላችሁ፦ ጨዋታ፣ ዘፈን፣ ውዝዋዜ ማስተማር ትችላላችሁ። ስለ ስፖርት፣ ስለ እንስሳት ወይም ስለሌላ መስክ እውቀትን ማካፈል ትችላላችሁ። አስተማራችሁ? ተማራችሁ? አሁን በሚናዎቻችሁ ተቀያየሩ።
ረዥሙመንገድ
ጨዋታ - እንዴት እዚያ መድረስ ይቻላል?
በማዳመጥ እገዛ ከቦታ ወደ ቦታ እንዴት መድረስ ይቻላል? ዓይናችሁን ጨፍናችሁ በክፍሉ በር ላይ ቁሙና አንዱን የቤተሰብ አባል በመመሪያ እገዛ በመተማመን ቤት ውስጥ ወዳለ ሌላ ቦታ እንዲመራችሁ ጠይቁ። መጽሐፉን ተከትላችሁ ለእናንተው ያዘጋጀነውን የቦርድ ጨዋታ በመጫወት መቀጠል ትችላላችሁ።
ረዥሙመንገድ
ረዥሙመንገድ