אמפתיה
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ግንኙነት
ከዚህ በፊት ስለተዋወቃችኋቸው ወይም ስለምታውቋቸው አረጋውያን መናገር ትችላላችሁ። እነማን ነበሩ? ከዚህ በፊት ከእነርሱ ጋር ያላችሁ ግንኙነት ምን ነበር? አሁን አንድ ላይ ምን ማድረግ ይወዳሉ? እናንተ ወላጆች፣ ከልጅነታችሁ ጋር አብረው ሲሄዱ ከቆዩ ገፀ ባህርያት ምን ትዝታ አላችሁ?
የልደት ቀን አለን
ታሪክ መስማት
ታሪኩን ማዳመጥ ይፈልጋሉ? ኮዱን ስካን በማድረግ መጽሐፉን እያገላበጡ ቤት ውስጥ፣ እየተጓዙ ወይም በፈለጋችሁት ጊዜ ታሪኩን አብራችሁ ማዳመጥ ትችላላችሁ።
የልደት ቀን አለን
"ጌታዬ ንጉስ ሆይ ሰላም"
አሚራ በአንድ ወቅት የተጫወተችውን ጨዋታ ለመጫወት አስባለች – እናንተም ትችላላችሁ! እንዴት ነው የምንጫወተው? ከተሳታፊዎቹ አንዱ “ንጉሱ” ሲሆን የተቀሩት ደግሞ በፊቱ መጥተው “ሰላም ጌታዬ ንጉስ ሆይ!” የሚሉ “ልጆቹ” ናቸው። ንጉሱም መልሶ “ሰላም ውድ ልጆቼ! የት ነበራችሁ? ምንስ እያደረጋችሁ ነበር?” ልጆቹ የት እንደነበሩና ምን እንዳደረጉ ያለ ቃላት የሰውነት እንቅስቃሴዎችንና የፊት ገጽታዎችን በመጠቀም ማብራራት አለባቸው። ንጉሱም መገመት አለበት። ሚናዎችን መቀየር ይቻላል፤ የሚፈለግም ነው።
የልደት ቀን አለን
የድግስ ሰበብ
ዓልማ በአስማታዊ ቆብና አስደናቂ መጠጥ የጠንቋዮች ድግስ አቅዳለች። ጠንቋዮችና አስማተኞች እንዲቀላቀሉ ጋብዛለች። እናንተም አስማታዊ ድግስ ለማዘጋጀት ማቀድ ትችላላችሁ… በራሳችሁ አስማታዊ ሃሳቦች። ምናልባትም የበዓል ድግስ? የጨዋታ ድግስ? ወይስ በሌላ ርዕስ ላይ የምትወዱት ድግስ?
የልደት ቀን አለን
ከትንሽ እስከ ትልቅ
አባዬ ትልቅ ጫማ አለው፣ የእማዬ ጫማ – ትልቅ አይደለም፣ ያኤሊ ትንሽ ጫማ አላት፣ እና የኤሊክ ቤሊክስ? ጥቃቅን ጫማዎች! በቤቱ ውስጥ በሙሉ ጉዞ ይሂዱ፣ ተመሳሳይ አይነት እቃዎችን ይሰብስቡ እና ከትንሽ እስከ ትልቁ ያዘጋጁዋቸው።
ኤሊክ ቤሊክ
አብሮ ማንበብ
እንዲሁም ቤትዎን የሚጎበኙ ትናንሽ ጓደኞች አሉዎት? ምናባዊ ጓደኞች ናቸው፣ ወይም ምናልባት ተወዳጅ አሻንጉሊት? ከታዳጊዎች ጋር ስለ ጉዳዩ ማውራት እና ከትንሽ ጓደኛው ጋር ምን ማድረግ እንደሚወዱ መስማት ጠቃሚ ነው። ታሪኩን ለመቀላቀል እና ለማንበብ ትንሹን ጓደኛውን “ማምጣት” ይችላሉ።
ኤሊክ ቤሊክ
ታሪኩን እንዴት ማንበብ ይቻላል?
ታሪኩ ከወትሮው ትንሽ ረዘም ያለ ነው፣ እናም ፍላጎትን እና የማወቅ ጉጉትን ለመቀስቀስ በተለያዩ ድምጾች መንገር ይመከራል፦ በአባ ድምጽ፣ በያኤሊ ድምጽ እና የተለየ በእማማ እና በኤሊክ ቤሊክ ድምጽ። ስዕላዊ ማብራሪያዎችን አንድ ላይ ማየት እና ታዳጊዎች ዝርዝሮችን በመለየት ላይ እንዲሳተፉ እና “ኤሊክ ቤሊክ (Elik Belik)” የሚሉትን ቃላት እንዲግሙ መጋበዝ ይችላሉ።
ኤሊክ ቤሊክ
የድብብቆሽ ጫወታ
አሻንጉሊቱ የት አለ? ጠረጴዛው ላይ? ምናልባት ከእርሱ ስር? እና ኳሱ የት አለ? የተለያዩ ነገሮችን መደበቅ፣ እነርሱን መፈለግ እና ከዚያ የሚከተሉትን ማለት ይችላሉ፦ “ኳሱ ወንበር ላይ ነው”፣ “ኳሱ በአልጋው ስር ነው”። እንዲሁም ራስዎን መደበቅ እና እርስ በርስ መፈላለግ ትችላላችሁ።
ኤሊክ ቤሊክ