ערבות הדדית
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ለቤተሰብ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር
በጋራ ማንበብ ሴቶችና ወንዶች ልጆች በታሪኩ ውስጥ የተለያዩ ገጸ-ባህርያት ያላቸውን እንዲለዩ ያስችላቸዋል። መለየቱ ሲመሰረት ለሌላው እንደ መራራትና መተሳሰብ ያሉ ውስብስብ ስሜቶች ላይ መወያየት ይችላሉ።
ጓደኛ ጓደኛን ይቀይራል
ውይይት - ለእርሱ ... እናት ብሆን
በቤተሰብዎ ውስጥ የእያንዳንዷና የእያንዳንዱ ሚናዎች ምንድን ናቸው? ከማን ጋር መለዋወጥ ይፈልጋሉ? በመጽሐፉ መንፈስ ውስጥ በቤተሰብ ውስጥ ያሉ ሚናዎችን መቀየር ላይ አብረው መገመት ይችላሉ – ልጆቹ ከአያት ጋር ቢቀያየሩ ምን ያደርጋሉ? አያትስ ከእናት ጋር ቢቀያየር ምን ያደርጋል? እንዴትስ እርስ በርሳችሁ መረዳዳት ትችላላችሁ?
ጓደኛ ጓደኛን ይቀይራል
ታሪኩን ማዳመጥ
በሰልፉ ውስጥ ምን መጫዎት ይቻላል? በኦርኬስትራ ውስጥ ያሉ መሳሪያዎች እንዴት ይሰማሉ? – እነዚህ ሁሉና ሌሎችም ኮዱን ስካን በማድረግ ታሪኩን ሲያዳምጡ ይጠብቁዎታል።
ጓደኛ ጓደኛን ይቀይራል
ጨዋታ – ሙያዬ ነው
ገጸ ባህርይው ማን ነው፦ ዶክተር ወይስ ምናልባት ቀልደኛ? – በእያንዳንዱ ዙር ተሳታፊዎች አንድ ባለሙያን ይመርጡና በትወና አቅርበው ተሳታፊዎቹ ገጸ ባህርይው ማን እንደሆነ መገመት አለባቸው። ለመገመት ትንሽ ይከብዳል? – ፍንጭ መስጠት ይቻላል።
ጓደኛ ጓደኛን ይቀይራል
ወደ ሥዕላዊ መግለጫዎች መግባት
በታሪኩ ውስጥ ከማን ጋር መለዋወጥ ይፈልጉ ነበር? መጽሐፉን ማገላበጥ፣ መቀየር የሚፈልጉትን ሰው መምረጥና እርስ በርስ መጋራት ይችላሉ፦ ጋጋሪውን መቀየር ይፈልጋሉ? በሰልፍ ውስጥ የሚጫወተውን?
ጓደኛ ጓደኛን ይቀይራል
ጓደኛ ጓደኛን ይቀይራል
ውይይት - ግምት ውስጥ ማስገባት
ግምት ውስጥ ስለማስገባት መወያየት ይችላሉ-“ግምት ውስጥ ማስገባት ” ምንድን ነው? በታሪኩ ውስጥ ማንን ማን ግምት ውስጥ አስገባ? – አንድ ሰው እርስዎን ግምት ውስጥ ያስገባበትን አጋጣሚዎች ማካፈል አስፈላጊ ነው – ምን ሆነ ምንስ ተሰማዎት? በቤተሰብስ ውስጥ እርስ በርስ መተሳሰብ የሚቻለው እንዴት ነው?
ይህ ያገባኛል ያለው ጃርት
משחק – מצאו אותי!
የጃርቱን ቤት የሚያሳየውን ሥዕላዊ መግለጫ ይመልከቱ።
በእያንዳንዱ ዙር ከተሳታፊዎቹ አንዱ በሥዕላዊ መግለጫው ላይ ያለውን ነገር ይጠቁማል። ይህ ነገር በእርስዎ ቤት ውስጥ የት አለ? ሌሎች ተሳታፊዎች እንዲያገኙት ይጋበዛሉ።
ይህ ያገባኛል ያለው ጃርት
እንስሳትና ሥዕላዊ መግለጫዎች
የመጽሐፉ ጀግኖች ጃርት፣ ጥንቸልና አይጥ ናቸው። በመጽሐፉ ውስጥ በተገለጹት ሥዕላዊ መግለጫዎች ውስጥ ብዙ እንስሳት ይታያሉ – ልታገኟቸው ትችላላችሁ? ስንት እንስሳት አገኛችሁ?
ይህ ያገባኛል ያለው ጃርት