התחלה
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ለንባብ ጠቃሚ ምክር፦ ከመጽሐፍ ጋር ጓደኝነት መፍጠር
ከትንሽነታቸው ጀምሮ መጻህፍትን ማንበብ ለጨቅላ ሕፃናት እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል። በዝግታና ቀስ በቀስ ማንበብ መጀመር ይመከራል። መጀመሪያ ላይ ታዳጊው በራሱ መንገድ ከመጽሐፉ ጋር መገናኘት ይችላል፦ ይዳስሰዋል፣ ይከፍተዋል ይዘጋዋል፣ ምስሎችን ይመለከትና ለማወቅ ይጓጓል። ከዚያ ማንበብ ይችላሉ፦ በየቀኑ ትንሽ፣ በትዕግስትና በእርጋታ ማንበብ። አንድ ገጽ ብቻ ማንበብ የሚመርጡ ታዳጊዎች አሉ፣ ማዎቅ፣ ማለማመድና እነሆ – መጽሐፉ ጓደኛ ሆኗል!
አንድ ትንሽ ልጅ ወደ መዋእለ ህጻናት ሄደ
በመንገድ ላይ ምን ይከሰታል
ትኩረት የምንሰጥ ከሆነ አስደሳች ግኝቶችን ማግኘት ይቻላል። በመንገድ ላይ ስለሚያዩት ነገር፣ በእግር ወይም መኪና ሲነዱ ማውራት ይችላሉ። “ቀይ መኪና ይኸውና!” “ደመና አያለሁ አንተስ ምን ታያለህ?” እንዲሁም ከታዳጊዎች ጋር መካፈልና ልምዶችን መለዋወጥ ይችላሉ፦ “ወደ ሥራ መንገድ ላይ አንዲት ሴት ከውሻ ጋር ስትራመድ አየሁ ዛሬ ወደ ሕጻናት ማቆያው ወይም ከእርሱ ስትመለስ ምን አየህ?”
አንድ ትንሽ ልጅ ወደ መዋእለ ህጻናት ሄደ
የጠዋት ሥነ ሥርዓት
በመጽሃፉ ውስጥ እንዳለው ልጅ, ታዳጊዎችም እንዲሁ መደበኛ አሰራርን የሚፈጥሩ የአምልኮ ሥርዓቶች ይወዳሉ, የሚያረጋጉ እና ቀኑን በጥሩ ስሜት እና ደስታ እንዲጀምሩ ይረዷቸዋል. ጠዋት ላይ የእራስዎን ትንሽ የጠዋት ሥነ ሥርዓት ማካሄድ ይችላሉ – ለምሳሌ, ታዳጊው ለተወዳጅ ቴዲ ድብ እንዲሰናበት ማበረታታት ይችላሉ: “ዱቢ, ቴዲ, ወደ ኪንደርጋርተን እሄዳለሁ, ሰላም!” እና እርስዎ, ወላጆች, በድብ ስም መልስ ይሰጣሉ: “ሰላም, ሰላም እና በረከት! እና የተሳካ መንገድ!”
አንድ ትንሽ ልጅ ወደ መዋእለ ህጻናት ሄደ
ከእንስሳት ጋር መገናኘት
በመጽሐፉ ውስጥ ብዙ እንስሳት ይታያሉ። አንድ ላይ ሆነው እነርሱን በመመልከት ስማቸውን መጥቀስ፣ የእንስሳትን ድምፅ ማሰማት ወይም እንቅስቃሴያቸውን ማስመሰል ትችላካችሁ። እንደ ዶሮ መጮህ፣ እንደ ጥንቸል መዝለል ወይም እንደ ፈረስ መጋለብና መጮህ ይችላሉ። እንዲሁም በመጨረሻው ገጽ ላይ ያሉትን ምስሎች በመመልከት በእያንዳንዱ ጊዜ ከእንስሳቱ ውስጥ አንዱን በመደበቅ የሚሰማውን ድምጽ በማሰማት ወይም እንቅስቃሴውን በማስመሰል ታዳጊው የትኛው እንስሳ እንደሆነ እንዲገምት መጠየቅ ይችላሉ።
አንድ ትንሽ ልጅ ወደ መዋእለ ህጻናት ሄደ
የንባብ ምክር
መጽሐፉን ወደ ጓደኛ እንዴት ይለውጡታል? ከልጅነት ጀምሮ መጽሐፍትን ማንበብ ለታዳጊ ሕፃናት እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ በረክታል። የእኛ ምክር በዝግታ፣ ቀስ በቀስና ለታዳጊ ሕፃን ተስማሚ በሆነ መንገድ መጀመር ነው፡- አንዳንዶች መጽሐፉን መንካት፣ መክፈትና መዝጋት ወይም እንዲያውም “መቅመስ” ሁሉ ይፈልጋሉ። ከዚያ ትንሽ በትዕግስትና በደስታ ማንበብ ትችላላችሁ። ገጽ አንድ ጀምራችሁ አንብቡ፣ ተላመዱት፣ ገፆች ጨምሩበት፣ እነሆም – መጽሐፉ ጓደኛ ሆኗል…!
ደህና አደራችሁ!
"አንድ ላይ ማንበብ - "ደህና አደራችሁ
በንባብ ጊዜ “እንደምን አደራችሁ” የሚሉትን ቃላት በልዩ ድምጽና በሠላምታ አሰጣጥ ምልክት አፅንዖት መስጠት ይችላሉ። ታዳጊውን እንዲቀላቀል፣ ታሪኩን እንዲከታተልና የንባብ አጋር እንዲሆን ይጋብዙት። የእራስዎን ሥነ ሥርዓት መፍጠርና “ደህና አደራችሁ”ን መመኘት ይችላሉ። “ደህና አደራችሁ በኩሽና ውስጥ ላለው ወንበር!”፣ “ደህና አደራችሁ በመንገድ ላይ ላለው ዛፍ!”፣ “ደህና አደራችሁ” ለውሻው ቦቢ!”
ደህና አደራችሁ!
ዓለምን መመልከት
በታዳጊ ህጻናት እይታ ሁሉም ነገር ስለ ዓለም የሚያስተምር ድንቅ ነገር ነው። ወደ መዋእለ ሕጻናት በሚሄዱበት ጊዜ ወይም ከመውጣትዎ በፊት የሚኖረው ጊዜ የሕፃኑን ትኩረት የሚስበውን በጋራ ለመመልከት እድል ነው። በመስመር ላይ የሚራመዱ ጉንዳኖች፣ ትልቅ የጭነት መኪና፣ ምናልባትም በሰማይ ላይ የሚበሩ የወፎች መንጋ?
ደህና አደራችሁ!
ደህና አደራችሁ!
ማንበብ፣ መዘመር እና መንቀሳቀስ
ታዳጊው የሚደጋገመውን ዓረፍተ ነገር ያጠናቅቀው፦ “ወዴት፣ ወዴት? ወደ መዋዕለ ህፃናት!”
እንቅስቃሴዎችን መጨመር፣ ማጨብጨብ ወይም የሙዚቃ መሳሪያዎችን መጠቀም ይችላሉ።
ወዴት? ወደ መዋዕለ ህፃናት!
የጠዋት ስነ-ስርአታችን
ተደጋጋሚ የጠዋት ድርጊቶች ታዳጊዎች ቀኑን በጥሩ ሁኔታ እንዲጀምሩ ይረዳቸዋል፦
ልብሱን አብሮ ማዘጋጀት፣ አስደሳች መዝሙር መዘመር፣ በመንገድ ላይ ቅጠሎችን ወይም ቀንበጦችን መሰብሰብ፣ ወይም ቋሚ በሆነ የሚያበረታታ ሰላምታ ቻዎ ማለት።
ወዴት? ወደ መዋዕለ ህፃናት!
ስዕላዊ ማብራሪያዎች ተረትን ይናገራሉ
አንድ ላይ ይመልከቱና ታዳጊው እንዲያገኝ ያድርጉ፦ ወፏ የት አለች? በተጨማሪ ገጾች ላይ ነውን? ልጁን ወደ መዋዕለ ህፃናት የሚሸኘው ማነው? ወደ መዋዕለ ህፃናት እንዴት እንሄዳለን – በብስክሌት፣ በእግር ወይም በሌላ መንገድ? ኮፍያ የሚለብሰው ማን ነው እና ውሻው የት አለ?
የመጨረሻውን ገጽ ይመልከቱ እና ይጠይቁ፦ “በመዋዕለ ሕፃናት ውስጥ ያሉ ልጆች ምን እያደረጉ ነው? በመዋዕለ ሕፃናት ውስጥ ምን ማድረግ ትወዳለህ/ትወጃለሽ?
ወዴት? ወደ መዋዕለ ህፃናት!
ጨዋታ፦ ወዴት?
ይጠይቁ፦ ወዴት፣ ወዴት? እና በእያንዳንዱ ጊዜ የተለየ ቦታ ይምረጡ፦ ወደ… መታጠቢያው፣ በረንዳው ወይም ወደ… የመጫወቻ ስፍራው? ወደ መረጡት ቦታ አብራችሁ ሂዱ፣ እርስ በርሳችሁ ተቃቀፉ እና ከዚያም ጮክ ብላችሁ ተናገሩ፦ ወዴት? ወዴት? ወደ… የሚቀጥለው ቦታ!
ወዴት? ወደ መዋዕለ ህፃናት!
ወዴት? ወደ መዋዕለ ህፃናት!