דמיון וחלום
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
መለየትና መጠቆም
እነሆ ባሕሩ! ተራራውም! ቢራቢሮም አለ! ታዳጊዎቹ አድገው በሥዕሉ ላይ የሚያውቁትን በጣታቸው መጠቆም ደስ ይላቸዋል። በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ቆም ብለው መመልከት፣ መረዳትና ማወቅ ይችላሉ። ታዳጊዎቹ ምን ያውቃሉ? “ጥንቸሉ የት አለ?” ብለው መጠየቅ ይችላሉ። ትንሽ አስቸጋሪ ከሆነም አንድ ላይ መፈለግ ይችላሉ።
ጥንቸል በባቡር ላይ ተቀምጣለች
ከመጽሐፉ ወደ ዓለም መውጣት
ባቡሩ በመጽሃፉ ውስጥ ይጓዛል። በቤትዎም ጉዞውን መቀጠል ይችላሉ፦ በጉልበቶችዎ በመቀመጥ “ቱ ቱ ቱ” በሚለው ጥሪና እንቅስቃሴን በመጨመር ወይም ምንጣፍ ላይ ከአንዳንድ አሻንጉሊቶች ጋር በመሆን። እንዲሁም በመስኮቱ ላይ ሆነው አብረው ማየት ይችላሉ። ውጭ ምን እየተፈጠረ እንዳለ ለማወቅና “የትራፊክ መብራት ይሄውና! ዛፍ ይሄውና! ሌላስ ምን ታያላችሁ?” ለማለት ይቻላል።
ጥንቸል በባቡር ላይ ተቀምጣለች
ለንባብ ጠቃሚ ምክር፦ ድምፅንና የፊት መግለጫዎችን መጠቀም ለንባብ እንዴት ይረዳል?
ታዳጊዎች በሚያነቡበት ጊዜ በድምፅ ቃና፣ ፊት ላይ በሚነበቡ ስሜቶች፣ ድምፆችና እንቅስቃሴዎች ይማረካሉ፦ እነዚህ ሁሉ ተረቱን እንዲከታተሉ፣ እንዲዝናኑበትና እንዲረዱት ያግዛቸዋል። እራስዎን ለጥቂት ደቂቃዎች ተዋናይ እንዲሆኑ ይፍቀዱ፤ ልዩ ንባብዎን እንዴት እንደሚያደንቁና እንደሚዝናኑ የሚያውቁ ምርጥ ታዳሚዎች አሉዎት።
ጥንቸል በባቡር ላይ ተቀምጣለች
ለቤተሰባዊ ንባብ ጠቃሚ ምክር
የጋራ ንባብን አስደሳች ለማድረግና ንባብን ለማበረታታት ወንድና ሴት ልጆችን የሚያናግርና ከልባቸው ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የሚዳስሰውን መጽሐፍ መምረጥ አለብዎት፦ አንዳንዶቹ ምናባዊ ታሪክን ይመርጣሉ፣ ሌሎች ደግሞ “በእውነት የተከሰተ” የሚልን መጽሐፍ ማንበብ ይፈልጋሉ። እያንዳንዱ ተወዳጅ ታሪክ በመጻሕፍት መደሰትን እንዲቀጥሉ ያበረታታቸዋል፤ ምናባቸውንና የፈጠራ ችሎታቸውንም ያዳብራል።
ማሽኑ
ውይይት - ዕቃዎችና ትውስታዎች
እንዲሁም ካለፉት ጊዜያት ያጋጠሙዎትን ነገሮች የሚያስታውሱ ነገሮችን መፈለግ ይችላሉ፦ የቤተሰብ ፎቶ፣ የተቀበሉት ስጦታ ወይም ካገኙት ልምድ ጋር የተያያዘ እቃ። እያንዳንዱ በተራው የመረጠውን ነገር ያቀርባል፤ ከእርሱም ጋር የተያያዘውን ትውስታ ያጋራል።
ማሽኑ
ታሪኩን ማዳመጥ
ወንድ አያት እንዴት ይሰማል? ማሽኑ ድምጾችን ያሰማል? – ኮዱን ስካን ካደረጉ ታሪኩን አንድ ላይና በተናጠል ማዳመጥ ይችላሉ።
ማሽኑ
የሆነ ነገር መገንባት
የራስዎ የሆነ ማሽን ይፈልጋሉ? – የቆዩ ሳጥኖችን፣ ጨርቆችን፣ ካርቶኖችንና መጫወቻዎችን በመሰብሰብ የራስዎን ማሽን መገንባት ይችላሉ። ምን እንደሚሰራና ምን እንደሚመስል አብረው ማቀድ የሚችሉ ሲሆን እንዲሁ መገንባትና በዚያው ማግኘትም ይችላሉ።
ማሽኑ
ስዕላዊ መግለጫዎች - ማሽኖቹ የት አሉ?
በመጽሐፉ ውስጥ ያሉት አብዛኛዎቹ ስዕላዊ መግለጫዎች ማሽኖችን ያሳያሉ። መጽሐፉን በማገላበጥ የማሽኖችንና ክፍሎቻቸውን ስዕላዊ መግለጫዎች መፈለግ ይችላሉ – የማሽኑ ሚና ምን እንደነበረ ታውቃላችሁ? ምናልባትም ያገኙትን ክፍል ተከትሎ አዲስ ማሽን መፍጠርና ምን እንደሚሰራ መገመት ትችሉ ይሆናል።
ማሽኑ
ማሽኑ
ውይይት - ችግርና መፍትሄ
ችግር ሲያጋጥማችሁ ምን ታደርጋላችሁ? – እናንተው ወላጆች የገጠማችሁን ችግር ለሴቶችና ወንዶች ልጆች ማጋራት ትችላላችሁ። ምን እንደተሰማችሁ እንደገና ለማጠንጠን ሞክሩ፤ ሊሆኑ ስለሚችሉ መፍትሔዎችም አብራችሁ አስቡ። ከዚያም ችግሩ እንዴት እንደተፈታ ተርኩ።
ስለ ድንክዬዎች፣ እንጉዳዮችና ሌሎችም መጽሐፍ
በ... ምን ሊደረግ ይችላል?
የተፈለገው መሪ ወይም ሳህን ወይም … ሊሆን ይችላል – ኮዱን ስካን በማድረግ ስለ ፈጠራ ቪዲዮ ማየት ይችላሉ! ከዚያ አንድ ላይ ማሰብዎን ይቀጥላሉ – በጥቅልል ወረቀት ምን ሊደረግ ይችላል? በመሃረብስ? በድንክዬ አሻንጉሊትስ?
ስለ ድንክዬዎች፣ እንጉዳዮችና ሌሎችም መጽሐፍ
በጋራ መዘመር
ድንክዬዎቹ እንጉዳዮችን በመትከል “የሚያውቋቸውን ሁሉንም ዘፈኖች ዘምረዋል” – እርስዎም የሚወዷቸውን ዘፈኖች አንድ ላይ መዘመር ይችላሉ። ስለ ድንክዬዎቹ፣ ስለ ዝናብ ወይም ስለሚያበረታታዎትና ስለሚያስደስቱዎት ዘፈኖች መዘመር ይችላሉ።
ስለ ድንክዬዎች፣ እንጉዳዮችና ሌሎችም መጽሐፍ
ጨዋታ - እኔ የትኛው ድንክዬ ነኝ?
በእያንዳንዱ ዙር ከተሳታፊዎቹ አንዱ በመጽሐፉ ውስጥ የሚታየውን ድንክዬ ሆኖ ይተውናል- ጥላ የያዘውን ድንክዬ፣ እንጉዳይ የሚተክለውን ድንክዬ ወይም በኩሬ ውስጥ የሚዘለውን ድንክዬ። ሌሎቹ ተሳታፊዎች ድንክዬው ምን እየሰራ እንደሆነ መገመትና በመጽሐፉ ገፆች መካከል ማግኘት አለባቸው።
ስለ ድንክዬዎች፣ እንጉዳዮችና ሌሎችም መጽሐፍ
ስለ ድንክዬዎች፣ እንጉዳዮችና ሌሎችም መጽሐፍ
አብሮ ማንበብ
እያነበቡ ሳለ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ እጆችን ማካተት፣ መንገዳቸውን መከተል እና እንቅስቃሴያቸውን በማስመሰል ጠቃሚ ነው። ወላጆች እና ታዳጊዎች ባንድነት ሆነው ይህንን ማድረግ ይችላሉ፦ እጅን በጣት ጫፍ ላይ “ያራምዱ”፣ እጅ እንዲዘል ያድርጉ፣ በሥዕሉ ላይ ያለውን በር ያንኳኩ እና የመጽሐፉን አጠቃላይ ንቁ አንባቢ ይሁኑ።
ስለ እጅ የሚገልፀው መጽሐፍ
የእጅ ጨዋታዎች
በእጅ መጫወት በጣም አስደሳች ነው! እያንዳንዱ ሰው በተራው አንድ የተወሰነ እንቅስቃሴ ያደርጋል፣ የተቀሩት ተሳታፊዎች ደግሞ ይኮርጃሉ። እጆችዎን ማጨብጨብ፣ ሰላም ወይም ደህና ሁኑ ብለው ማወዛወዝ፣ ለ “ዝምታ” ምልክት ማሳየት ወይም መብረር ይችላሉ!
ስለ እጅ የሚገልፀው መጽሐፍ
የእጆች ቤተሰብ
ትንሽ እጅ ያለው ማነው? ትልቅ እጅ ያለው ማነው? እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል እጁን በወረቀት ላይ እንዲያስቀምጥ ይጋበዛል። እርስዎ፣ ወላጅ፣ የእጆችን ቅርጽ ይሳሉ፣ እና ታዳጊዎች ያጌጣሉ እናም ይሳያሉ። የሁሉም እጆች ምስል እንደ ማስታወሻ ሊቀመጥ ይችላል፣ እናም እንቅስቃሴውን ከአመት አመት መድገም እና ምን እንደተለወጠ ማየት ይችላሉ።
ስለ እጅ የሚገልፀው መጽሐፍ
የሚዘምሩ እጆች
እንደ “አስር ጣቶች አሉኝ (I have ten fingers)” ወይም “ኮፍያዬ ሶስት ማዕዘን አለው (My hat has three corners)” በመሳሰሉት የእጅ እንቅስቃሴዎች የታጀቡ መዝሙሮችን መዘመር ይችላሉ። ወደ መዝሙርዎ የእጅ ምልክቶችን ማከል ጥሩ ሀሳብ ነው፣ እናም በሌሎች ተወዳጅ መዝሙሮች ላይ የጣት እንቅስቃሴዎችን ማከል ይችላሉ። ይዝናኑ!
“עשר אצבעות לי יש” מאת רבקה דוידית
מחרוזת שירי ידיים מאת דתיה בן דור
ስለ እጅ የሚገልፀው መጽሐፍ
Pinterest – እደ ጥበቦች፣ መዝሙሮች እና እንቅስቃሴዎች በ Sifriyat Pijama በ Pinterest ገጽ ውስጥ።
ስለ እጅ የሚገልፀው መጽሐፍ
ውይይት - በምናብ አብሮ ማሰብ
ወንድና ሴት ልጆች የምናብ ጨዋታዎችን መጫወት ይወዳሉ። አዋቂ መስሎ መኪና ለ”መንዳት” መሞከር፣ ከጭቃ “ኬክ” መስራትና ከምናባዊ ጓደኛቸው ጋር መጫወት ያስደስታቸዋል። እንደ አሻንጉሊት፣ ድስት ወይም የመጫዎቻ መኪና ባሉ ነገሮች ዙሪያ ከልጆች ጋር አብሮ መጫወትና መጠየቅ ይቻላል – ወደየት እየሄድን ነው? አብረን ምን እናብስል? አሻንጉሊቱ ምን ይላል?
ምስል
ፈጠራ - በውሃ ውስጥ ያለ ነጸብራቅ
ነጸብራቅ መስራት ይፈልጋሉ? በኩሬው ውስጥ እንደሚያዩት? – የኪው አር ኮዱን ስካን በማድረግ ለቀላል ፈጠራ መነሳሻን ማግኘት ይችላሉ።
ምስል
ጨዋታ - ራሱን ቁጭ
ሮን በኩሬው ውስጥ አንድ ምስል ተመለከተ፤ ነገር ግን በእውነቱ በውሃው ውስጥ የሚንፀባረቀው የራሱ ምስል ነው። የ”መስታወት” ጨዋታን መጫወት ይችላሉ። ሁለት የቤተሰብ አባላት እርስ በእርሳቸው ፊት ለፊት ይቆማሉ፦ በተራው መሰረት አንዱ “የፊት ቅርጽ” እየሰራ ጭንቅላቱን ወይም እግሩን ያንቀሳቅሳል፤ ሌላኛው ደግሞ እርሱን ለመምሰል ይሞክራል።
ምስል
እንቅስቃሴ - በኩሬ ውስጥ መዝለል
ከውጪ በኩል ኩሬዎች አሉ? – ቡትስ ጫማዎችን በማድረግ በደንብ ለብሶ ወደ ውጪ መውጣትና በኩሬ ውስጥ መዝለል ይችላሉ። መውጣት ተገቢ ካልሆነስ? – ከገመድ ወይም ከወረቀት “ኩሬ” መስራትና የፈለጉትን ያህል ወደ ውስጥና ወደ ውጪ መዝለል ይችላሉ…
ምስል
פינטרסט
עוד יצירות והשראה מחכים לכם בתיקיית הספר בפינטרסט של ספריית פיג’מה!
ምስል