דילוג לתוכן המרכזי בעמוד
የወሩ መጽሐፍ

የእኔ መስኮት እዚህ ነው


በ: ኒኖ ቢኒያሽቪሊ ምሳሌዎች: አቪያ ኮሄን

ዕብራይስጥ የማይገባት አዲስ ገቢ መሆን ቀላል አይደለም። ኒኖ መዝፈን ትወዳለች፤ ግን ወደ እስራኤል ሃገር ስትደርስ ዝምታን መርጣለች። የእርሷን ድምጽ እንደገና ማግኘት ትችል ይሆን? የዕድሜዋ አቻ የሆነቺው ጎረቤቷስ ምን ልትነግራት እየሞከረች እንደሆነ ትረዳ ይሆን? ስለ ዓሊያና በእስራኤል ውስጥ ስርን ስለ መትከል የሚናገር ታሪክ።

የእድሜ ክልል: ቅድመ ትምህርት ቤት

ከጆርጂያ ወደ እሥራኤል ዓሊያ ያደረገችው ኒኖ ዓለሟ በመሠረቱ ተለውጧል። አሁን የማታውቀውን ቋንቋ፣ የተለያዩ መልክዓ ምድሮችና አዲስ ጎረቤቶች መልመድ አለባት። በአስቸጋሪ ጊዜያት ወደ ቀድሞው ዓለምዋ በመርከብ ላይ ስትጓዝ ራሷን ታስባለች። ቀስ በቀስ ታላቅ የሙዚቃ ፍቅሯ መልሕቅ ይሆንላትና ድምጾቹም ሆኑ ዜማዎቹ በሁሉም ቦታ አብረው እንደሚሄዱ ትደርስበታለች። ሙዚቃ ባህሎችንና ዓለሞችን የማገናኘት፣ እኛን የማበረታታትና በሕይወት ጉዞዎች አብሮን የመሄድ ሃይል አለው።

“በሌላኛው ቋንቋ ማስረዳት በሚያቅተው ጊዜ በዜማ ሲጫወት – ሌላኛው በደንብ ይረዳል።”
(“ጼማሕ ጼዴክ” ወይስ ኦር ቶራ፣ኦሪት ዘፍጥረት)

ታሪኩን ተከትሎ የሚመጣ ቪዲዮ

ማተሚያ ቤት:

מ' מזרחי

የስርጭት ዓመት:

תשפ״ה 2024-2025