דילוג לתוכן המרכזי בעמוד

አንድየፈካጠዋት

በ: ኦራ አያል ምሳሌዎች: ኦራ አያል

"በተራሮች መካከል ባለው ሜዳ ላይ ጉዞ የሚያደርገው ማን ነው? አንድ የማታውቁት ልጅ።" በገጹ መጨረሻ ላይ ጩኸት የሚያሰማው ማን ነው? ወደ ቀጣዩ ገጽ ይግለጡና አንድ አስገራሚ ነገር ያገኛሉ- ኮፍያ፣ ውሻ፣ አዲስ ጓደኛ - ሁሉም በመንገድ ላይ ከልጁ ጋር ይቀላቀሉ። የታሪኩን ድንቅነት የሚጨምሩ ታላላቅ ምስሎች፣ ዜማዎችና ግጥሞች ያሉት የቆየና ተወዳጅ መጽሐፍ።

የእድሜ ክልል: ታዳጊዎች

“””ለሁለት ሰዓት ያህል በእግራቸው ተጉዘዋል
በድንገትም… በመንገድ ላይ ምን አገኙ?

ወደ አያት ቤት የሚወስደው መንገድ በዙሪያችን ስላለው ዓለም ለመዝናናትና ለመማር እድል ይፈጥራል። ቆም ብለን ከተመለከትን አስደሳች ነገሮችን ማግኘት ምናልባትም ከእነርሱ ጋር አብሮ መሄድ የሚያስደስቱ ጓደኞችን ማግኘት እንችላለን። ክላሲክ መጽሐፍ ‘አንድ የፈካ ጠዋት’ ግጥሞችን፣ ተደጋጋሚ ዓረፍተ ነገሮችንና አስገራሚ ምስሎችን አጣምሯል። ይህ ጥምረት ለታዳጊዎች ልምድን የሚፈጥር ሲሆን ግኝታዊ ጉዞ እንዲያደርጉ ይጋብዛቸዋል። ቀጥሎ ምን ይሆናል? በሚቀጥለው ገጽ ላይ ምን ይጠብቃችኋል? “

ታሪኩን ተከትሎ የሚመጣ ቪዲዮ

ማተሚያ ቤት:

ספרית פועלים

የስርጭት ዓመት:

תשפ״ד 2023-2024