טֶבַע וּסְבִיבָה
קיימות
לשתול? לנטוע? לטפח אתר? לנקות חוף? קיימות היא היכולת לשפר ולשמר את הסביבה, את משאבי הטבע ואת ערכי הטבע כך שיהיה אפשר ליהנות מקיומם לאורך זמן ובדורות הבאים. קריאת סיפורים על קיימות וקיום פעילויות בנושאים סביבתיים, מסייעים לפתח גישה חיובית לסביבה ולהקנות הרגלי חיים ירוקים כבר בגילים צעירים.
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
"መነጋገር አይጠቅምም፤ በድርጊት ማሳመን ይገባል"
የያሽካ ዓረፍተ ነገር ላይ ምን ማለት እንደሆነ በመጠያየቅ ስለ እርሱ ምን እንደሚያስቡ መወያየት ይችላሉ። በመጀመሪያ መወያየትና መፈለግ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜና በየትኞቹ ሁኔታዎች በድርጊት ማሳመን እንደሚፈልጉ መጠያየቅ ይችላሉ።
ለአካባቢያችን ስንል
በአካባቢዎ የሚወዱት የህዝብ ቦታ አለ? እርሱን ሲጎበኙ ለአፍታ ቆም ብለው ደስ የሚያሰኘውን ለአካባቢው ምን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትና እንዴት ሊድን እንደሚችል ማሰብ ይችላሉ። ለምሣሌ፦ ከቤተሰብና ከጓደኞች ጋር የጽዳት ወይም የማስዋብ ዘመቻ መጀመር ይችላሉ።
ኦሪጅናል ፈጠራዎች
አያት ያሽካ ልዩ ፈጠራዎችን ፈልስፏል። ሲተኙ የሚጠፋ የሌሊት ብርሃን ወይም የውሃ ውስጥ ወፍ መብረርያ። እርስዎንና ሌሎችን የሚረዱ ምን ምን ልዩ ፈጠራዎችን ይፈልጋሉ? ከቆሻሻ ቁሳቁሶች ልዩ ፈጠራዎችን በምናብ ማሰብ፣ መሳል ወይም መገንባት ይችላሉ።
האזינו לסיפור "סתם שדה ריק"
אנו מזמינים אתכם/ן להאזין להקלטה הקסומה של הסיפור “סתם שדה ריק”, מאת: תמר וייס-גבאי | איורים: בלה פוטשבוצקי | הוצאת: כנרת (גנים)
יוצרים ומגישים – ירדן בר כוכבא – הלפרין ודידי שחר מוזיקה ונגינה – טל בלכרוביץ’ פתיח – דידי שחר
מוכנים/ות? מת – חי – לים!
ውይይት - መተሳሰብ ምንድን ነው?
“አካባቢ ላይ መተሳሰብ አስፈላጊ ነው”- መተሳሰብ ምንድን ነው? በቤተሰብ አባላት መካከል በቤት ውስጥ አንዱ ለአንዱ እንዴት መተሳሰብ ይቻላል? በአካባቢስ እንዴት እንተሳሰብ? በዚህ ጉዳይ ላይ ከሴቶችና ወንዶች ልጆች ጋር መወያየት ትችላላችሁ፤ ሰዎችና አካባቢ ላይም እንዴት መተሳሰብ እንደሚቻል አስተያየት መስጠት ይችላሉ።
የምልከታ ግብዣ
በአካባቢው ያለውን የተፈጥሮ ክፍል ለመጎብኘት ተጋበዛችሁ፦ በቤቱ አጠገብ ያለን የአትክልት ቦታ፣ ሜዳ፣ ጓሮ ወይም በረንዳ ላይ ያለን የአበባ ማስቀመጫ። በጸጥታ ተቀምጣችሁ ብትመለከቱ ምን ታገኙ ይሆን? በአጉሊ መነጽር መታገዝ ይመከራል።
እርስበርስ መማር
አዋቂዎች ከወንዶችና ሴቶች ልጆች ምን ሊማሩ ይችላሉ? ብዙ ነገሮች! የሚወዱትን ጨዋታ በመጫዎት፣ ሥዕል በማዘጋጀት፣ በመዋዕለ- ህፃናት ውስጥ የተማሩትን ርዕሰ ጉዳይ በማዎቅ ወይም አስደሳች አስተሳሰብን በማካፈል። ወንዶች እና ሴቶች ልጆችስ ከአዋቂዎች ምን ሊማሩ ይችላሉ? አንዱ ከሌላው ምን መማር እንደሚችል ለማወቅ አብራችሁ መቀመጥ እና በትኩረት መከታተል ብቻ ያስፈልግዎታል።
ቀለሞችን መያዝ
ሰማዩ ሰማያዊ፣ መሬቱ ቡናማ፣ እፅዋቱ ደግሞ አረንጓዴ ናቸው። ወደ ውጭ መውጣትና “ቀለሞችን መያዝ” አለባችሁ። እያንዳንዱና እያንዳንዷ ሁሉም በተራ አንድ ቀለም ያሳውቁና ሌሎች ተሳታፊዎች በአካባቢው ውስጥ አንድ ያንኑ ቀለም ያለው እቃ በፍጥነት ማግኘትና ወደ እርሱ ማመልከት ይኖርባቸዋል።
የአባዬ መነፅር
አያት ያሽካ የባህር ዳርቻውን ያድናል
እንዲሁ ባዶ ሜዳ


