סיום ופרידה
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-

የቤተሰባዊ ንባብ ምክር
በእያንዳንዱ መጽሐፍ ውስጥ የሚወደድ ነገር አለ፦ በታሪኩ ውስጥ ያለው ውጥረት፣ ገፀ ባህሪያቱና ምናልባትም ምስሎች ወይስ ልዩ ቃላቱ? በንባቡ መጨረሻ ላይ ልጆች ስለ ታሪኩ የወደዱትን መጠየቅና እናንተው ወላጆችም የወደዳችሁትን አካፍሉ። በተለይ የትኞቹን መጽሃፎች እንደምትወዱና ለምን እንደሆነ እርስ በርሳችሁ መተረክ ትችላላችሁ።
በአትክልቱ ውስጥ ያለ እብጠት

እኛና ጓደኞች
ፊትዝና እንጉዳዩ አንድ ላይ ናቸው። እርሷ አትክልቶቹን ታበቅላለች፤ እርሱ ይንከባከባል። እስከዚያው ድረስ ይጨዋወታሉ፤ ይዘምራሉ፤ እንዲሁ አብረው ይዝናናሉ። ልጆችን ከጓደኞቻቸው ጋር ምን ማድረግ እንደሚወዱ መነጋገርና መጠየቅ እንችላለን። አብረው ጊዜ የሚያሳልፉት እንዴት ነው? ይህ ለወላጆች የልጅነት ጓደኞቻችሁን የማስታወስና ልምዶችን ከልጆችዎ ጋር ለመካፈል እድል ነው።
በአትክልቱ ውስጥ ያለ እብጠት

አትክልቶችና ምስሎች
ጥቅል ጎመን? ብሮኮሊ? – በመጽሐፉ ውስጥ አሥራ ሦስት ዓይነት ለምግብነት የሚውሉ አትክልቶች ይገኛሉ፦ ልታገኟቸው ትችላላችሁ? ምናልባትም የሚወዱትን አትክልት መመገብ ወይም አዲስ አትክልቶችን መሞከርና መቅመስ ይፈልጋሉ?
በአትክልቱ ውስጥ ያለ እብጠት
አትክልቶችን ማሳደግ
ምንም እንኳን መሬት ባይኖራችሁም አትክልቶችን ማምረት ትችላላችሁ፦ የተቆረጠ የካሮት ራስ፣ የነጭ ሽንኩርት ወይም የሰላጣ ወይም የካርፓስ የታችኛው ክፍል ግልፅ አድርጎ በሚያሳይ መያዣ ውስጥ ውሃ ማጠጣት ይቻላል። በትዕግስት ይጠብቁ፤ አስፈላጊ ከሆነ ውሃ በመጨመር ቀስ በቀስ ሥሮችና ቅጠሎች እያደጉ ያገኙታል። መከርከምና መብላት ወይም በማሰሮ ውስጥ መትከል፣ ውሃ ማጠጣትና አዲሶቹን አትክልቶች እስኪያድጉ ድረስ መጠበቅ ይችላሉ።
በአትክልቱ ውስጥ ያለ እብጠት
ቪድዮ
እንጉዳይ አንተ ራስህ ማን ነህ? – ኮዱን ስካን በማድረግ በእስራኤል ውስጥ በየክረምቱ እንደ አዲስ ከሚታዩት እንጉዳዮች ጋር ያስተዋውቃል። የበለጠ መማር ይፈልጋሉ? አብረው ወደ ቤተ መፃህፍት በመሄድ ወይም በኢንተርኔት በማሰስ ስለ እንጉዳዩና ሌሎች እንጉዳዮች መረጃ ይፈልጉ።
በአትክልቱ ውስጥ ያለ እብጠት
በአንድ ወቅት ብቻውን መተኛት የማይፈልግ ልጅ ነበር
ድራማ – ታሪክ ከአሻንጉሊቶች ጋር
የልጆችዎ ተወዳጅ ፀጉር አሻንጉሊቶችና የእንስሳት መጫወቻዎች እንዲሁ የታሪኩ አካል ሊሆኑ ይችላሉ፦ በእያንዳንዱ ጊዜ የተለየ አሻንጉሊት እየጨመሩና እየቀነሱ ታሪኩን አንድ ላይ ይተውኑ።
በአንድ ወቅት ብቻውን መተኛት የማይፈልግ ልጅ ነበር
ጨዋታ - በብርድ ልብስ ውስጥ ማን ይተኛል?
ታዳጊው ሕጻን ዓይኖቹን ይዘጋና አሻንጉሊቷን እርስዎ ከብርድ ልብስ በታች ይደብቃሉ። ዓይኖቹን ሲከፍት እርስዎ ወላጆች ስለ እንስሳው ማንነት ፍንጭ ይሰጣሉ፤ ታዳጊው መገመት አለበት። ይጮኻል? ምናልባትም ይዘላል ካሮትስ ይበላል? ሚናዎችን መቀያየርና ታዳጊው እርስዎ በብርድ ልብስ ስር የደበቁትን ማን እንደሆነ እንዲጠቁማችሁ መፍቀድ ይችላሉ?
በአንድ ወቅት ብቻውን መተኛት የማይፈልግ ልጅ ነበር
በአንድ ወቅት ብቻውን መተኛት የማይፈልግ ልጅ ነበር