סבא וסבתא
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
טיפ לקריאה: משפט חוזר
ברבים מהספרים לפעוטות יש משפט חוזר שעוזר להם לעקוב אחר הסיפור ולהצטרף לקריאה. כדי להדגיש את המשפט החוזר בעת קריאת הסיפור תוכלו להקריא אותו בקול מיוחד, להוסיף תנועת ידיים או לשנות את קצב הקריאה. כשיגיע המשפט המוכּר להם ישמחו הפעוטות להצטרף אליכם.
አንድ ብሩህ ጠዋት
שיחה – את מי אנחנו אוהבים לבקר?
ביקורים הם חלק משמעותי מעולמם של פעוטות. אנחנו הולכים לביקור אצל קרובי משפחה וחברים, ולפעמים באים לבקר אותנו. תוכלו לשוחח ולשאול: את מי הלכנו לבקר? מה עשינו בזמן הביקור? את מי נזמין אלינו הביתה?
አንድ ብሩህ ጠዋት
משחק - את מי נפגוש עכשיו?
בקצה כל עמוד מופיע איור שרומז לפגישה שמחכה בעמוד הבא. לפני שהופכים את הדף תוכלו להביט ברמז המאויר ולנחש מי מחכה לכם בעמוד הבא. תוכלו גם לשחק עם חפצים אמיתיים: לכסות חפץ כמעט לגמרי ולשאול את הפעוטות מה מסתתר מתחת לכיסוי – דובון, כובע ואולי תיק קטן?
አንድ ብሩህ ጠዋት
מה באיור?
העמוד האחרון של הספר הוא סיפור בפני עצמו ובו פרטים מאוירים רבים. אפשר לחפש באיור את מי שפגשתם לאורך הסיפור: כלב, ילדה, כובע או פרח. אפשר גם לנסות לזהות חפצים בבית של סבתא ולקרוא להם בשם: היכן הקומקום? מה תלוי על הקיר?
አንድ ብሩህ ጠዋት
አንድ ብሩህ ጠዋት
ውይይት - የሴት አያት ታሪኮች
ወንድና ሴት አያቶች በልጅነታቸው፣ ጥቅም ላይ ስለዋሉና ከአሁን በኋላ ጥቅም ላይ ስለማይውሉ እቃዎች ታሪኮች ወይም ምናልባትም ሌላ ታሪክ? – ታሪኩን ተከትሎ ከወንድና ሴት አያቶች ጋር መነጋገርና ስላለፉት ቀናት ታሪኮችን ከእነርሱ መስማት ይችላሉ።
አያት ያለ ማጋነን ይተርካል
አያት ያለ ማጋነን ይተርካል
ጨዋታ - ምርጡ
አያት በጣም ደመቅ ያለ ሳቅና በጣም አስደሳች ታሪኮች አሉትና እርስዎስ በምን “ምርጥ” ነዎት? – እያንዳንዱ በተራው እርሱ በምን “ምርጥ” እንደሆነ ይናገራል። በሚቀጥለው ዙር ሁሉም ሰው ከጎኑ ያለውን ተሳታፊ በምን “ምርጥ” እንደሆነ ይነግራል – ግን በመልካም ነገሮች ብቻ!
አያት ያለ ማጋነን ይተርካል
ክብ ሰርቶ መደነስ
ለምንድነው ሁሉም ሰው የሚጨፍረው – የእስራኤል ሃገር በመቋቋሟ ሲሆን ይህም ለዳንስ ለመውጣት ትልቁ ምክንያት ነው። ዛሬ እስራኤል ስንት ዓመቷ እንደሆነ ያውቃሉ? ሃገሪቱ ከተቋቋመችስ ስንት ዓመታት አለፉ? እርስዎም ክብ ሰርተው አብረው ሙዚቃው ላይ መደነስና ዳንሱን ለአንድ ሰው ወይም ለሆነ ለተከሰተ ነገር ማበርከት ይችላሉ።
አያት ያለ ማጋነን ይተርካል
አያት ያለ ማጋነን ይተርካል
ለቤተሰባዊ ንባብ ጠቃሚ ምክር
የጋራ ንባብን አስደሳች ለማድረግና ንባብን ለማበረታታት ወንድና ሴት ልጆችን የሚያናግርና ከልባቸው ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የሚዳስሰውን መጽሐፍ መምረጥ አለብዎት፦ አንዳንዶቹ ምናባዊ ታሪክን ይመርጣሉ፣ ሌሎች ደግሞ “በእውነት የተከሰተ” የሚልን መጽሐፍ ማንበብ ይፈልጋሉ። እያንዳንዱ ተወዳጅ ታሪክ በመጻሕፍት መደሰትን እንዲቀጥሉ ያበረታታቸዋል፤ ምናባቸውንና የፈጠራ ችሎታቸውንም ያዳብራል።
ማሽኑ
ውይይት - ዕቃዎችና ትውስታዎች
እንዲሁም ካለፉት ጊዜያት ያጋጠሙዎትን ነገሮች የሚያስታውሱ ነገሮችን መፈለግ ይችላሉ፦ የቤተሰብ ፎቶ፣ የተቀበሉት ስጦታ ወይም ካገኙት ልምድ ጋር የተያያዘ እቃ። እያንዳንዱ በተራው የመረጠውን ነገር ያቀርባል፤ ከእርሱም ጋር የተያያዘውን ትውስታ ያጋራል።
ማሽኑ
ታሪኩን ማዳመጥ
ወንድ አያት እንዴት ይሰማል? ማሽኑ ድምጾችን ያሰማል? – ኮዱን ስካን ካደረጉ ታሪኩን አንድ ላይና በተናጠል ማዳመጥ ይችላሉ።
ማሽኑ
የሆነ ነገር መገንባት
የራስዎ የሆነ ማሽን ይፈልጋሉ? – የቆዩ ሳጥኖችን፣ ጨርቆችን፣ ካርቶኖችንና መጫወቻዎችን በመሰብሰብ የራስዎን ማሽን መገንባት ይችላሉ። ምን እንደሚሰራና ምን እንደሚመስል አብረው ማቀድ የሚችሉ ሲሆን እንዲሁ መገንባትና በዚያው ማግኘትም ይችላሉ።
ማሽኑ
ስዕላዊ መግለጫዎች - ማሽኖቹ የት አሉ?
በመጽሐፉ ውስጥ ያሉት አብዛኛዎቹ ስዕላዊ መግለጫዎች ማሽኖችን ያሳያሉ። መጽሐፉን በማገላበጥ የማሽኖችንና ክፍሎቻቸውን ስዕላዊ መግለጫዎች መፈለግ ይችላሉ – የማሽኑ ሚና ምን እንደነበረ ታውቃላችሁ? ምናልባትም ያገኙትን ክፍል ተከትሎ አዲስ ማሽን መፍጠርና ምን እንደሚሰራ መገመት ትችሉ ይሆናል።
ማሽኑ
ማሽኑ
ውይይት - የ"ድሮ" ታሪክ
መጽሐፉን ካነበቡ በኋላ ትዝታዎችን ማምጣትና የ”ድሮ” ታሪኮችን መተረክ ይችላሉ – በልጅነትዎ፣ በወላጆችዎ ወይም በወንድ አያትዎ ወይም በሴት አያትዎ ስለ ሩቅ ቀናት የተነገረ ታሪክን መተረክ ይችላሉ።
የናፍቆት ሳጥን
ታሪክ መስማት
ታሪኩን በጋራ ወይም በተናጠል ማዳመጥ ይችላሉ፦ ማድረግ ያለብዎት የኪው አር ኮዱን ስካን ማድረግና… መደነቁ ይጀምራል!
እንዲሁም ለአዲስ ገቢ ቤተሰቦች ተስማሚ ነው።
የናፍቆት ሳጥን
እንዴት አደግን!
ዛፉ አድጓል ርብቃም አድጋለች፣ እናንተስ? – ቪዲዮዎችንና ምስሎችን በማየት ልጆችና ወላጆች ምን ያህል እንዳደጉና እንደተለወጡ ማየት ይቻላል። ሴቶቹና ወንዶቹ ልጆች ሊያደርጓቸው ስለሚችሏቸውና ከዚህ በፊት ሊያደርጓቸው ስላልቻሏቸው ስራዎች መወያየት ይቻላል።
የናፍቆት ሳጥን
የብርቱካን ኬክ
ኬክ መሥራት ይፈልጋሉ? – ሁለት እንቁላል፣ አንድ ሶስተኛ ኩባያ ስኳር፣ አንድ ሶስተኛ ኩባያ ዘይት፣ ግማሽ ኩባያ የዕለት ብርቱካን ጭማቂ፣ አንድ ኩባያ ዱቄት (ወይም ምትክ) እና በሻይ ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር ያዘጋጁ። ከግማሽ ብርቱካን የተከተፈ ቅርፊት መጨመር ይችላሉ።
ንጥረ ነገሮቹን በቅደም ተከተል ያዋህዱና እስከ 180 ዲግሪ በሞቀ ምድጃ ውስጥ ለግማሽ ሰዓት ያህል ያኑሩት። መልካም ምግብ!
የናፍቆት ሳጥን
የናፍቆት ሳጥን
አብሮ ማንበብ
የታሪኩን ንባብ ለታዳጊዎች ማጋራት ተገቢ ነው፡- ቁልፉ የት ነው? በገመዱ ምን ያደርጋሉ፣ እና ፍርፋሪዎቹ ለምንድናቸው? በትንሹ ኪስ ውስጥ ምን አስገራሚ ነገር ተደብቋል?
የወንድ አያት ኪሶች
የመገመት ጨዋታ
በልብስ ኪስ ውስጥ ያለውን ነገር ይደብቁ እና የደበቁትን ነገር ህፃኑ በመዳሰስ ስሜት እንዲገምት ያድርጉ። ፍንጮችን ማቅረብ፣ የእቃውን ክፍልፋይ መግለጽ እና በመጨረሻም እቃውን ግልፅ ማድረግ እና ምን ጥቅም ላይ እንደሚውል ማሳየት ይችላሉ።
የወንድ አያት ኪሶች
በቤተሰብ ውስጥ ነገሮችን አብሮ ማድረግ
አያት እና ህጻኑ፣ ዘሮችን እየዘሩ እና ጥንቸሏን እየመገቡ፣ እያወሩ ናቸው። ታዳጊዎች በቤተሰብ ውስጥ ካሉ አዋቂዎች ጋር ምን ማድረግ ይወዳሉ? ከወንድ አያቶች እና ከሌሎች የቤተሰብ አባላት ጋርስ?
የወንድ አያት ኪሶች
ከምን ጋር ምን ይሄዳል?
“ለመክፈት ቁልፍ”፤ “ባቡር ለመሳፈር ትኬት”፤ ዘንቢልስ ለምንድን ነው? ወይስ ማንኪያ ለምንድነው? ቤት ዙሪያ መሄድ እና እቃዎችን መምረጥ፣ እናም ከዚያም ማውራት እና ምን ተብለው እንደሚጠሩ እና ምን ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ባንድነት ማረጋገጥ ይችላሉ። የማዛመድ ጨዋታ – ማን የማን ነው (Who Belongs to Whom) – ኮዱን ሲቃኙ እርስዎን እየጠበቀ ነው፦
የወንድ አያት ኪሶች
Pinterest – እደ-ጥበቦች፣ መዝሙሮች እና እንቅስቃሴዎች በ “የአያት ኪስ” መጽሐፍ ገጽ ላይ በ Pinterest ላይ በ Sifriyat Pijama ውስጥ
የወንድ አያት ኪሶች