אמנות ומוזיקה
סְּפָרִים
ለቤተሰባዊ ንባብ ጠቃሚ ምክር
ታዳጊ ሕጻናት የታሪኩ አካል መሆንን ይወዳሉ፦ በመጽሐፉ ውስጥ ያሉትን ቃላትና ድምጾች መድገም ወይም የመጽሐፉን ጀግኖች ድርጊት መተወን። በዚህ መንገድ ታሪኩን ይለያሉ፣ ስሜታዊ የሆነው ዓለማቸውን ያበለጽጋሉ፤ ቃላትንና ጽንሰ-ሐሳቦቻቸውን ያገኛሉ። ስለዚህ የጋራ ንባብ ላይ ጥሩምባን ይዞ “መንፋት”፣ ከበሮውን በእጆቻችሁ “መምታት” እና የሕብረት መዝሙሮች ላይ “መምራት” ይገባል።
ሙዚቃ
ውይይት
ጊሊ ለእርሷ የሚስማማ ሚና አግንታ ኦርኬስትራውን ትመራለች። እርሱን ተከትሎ በቤት ውስጥ ስለ ታዳጊ ሕጻናት ሚናዎች መወያየት ይችላሉ- ምን ያውቃሉና ምን ማድረግ ይፈልጋሉ – መጫወቻዎችን መሰብሰብ? ወለል መጥረግ? ለምግብ ጠረጴዛ ለማዘጋጀት መርዳት?
ሙዚቃ
ሙዚቃ
አብሮ መጫዎት
ማንኛውም ነገር ማለት ይቻላል የሙዚቃ መሳሪያ ሊሆን ይችላል፦ ወደ ዘፈኑ ዜማ እጆቻችሁን በአንድ ላይ ማጨብጨብ ወይም ያገኙትን የሙዚቃ መሳሪያዎች፣ ማራካሾችና መሳሪያዎች መሰብሰብ ይችላሉ። ማንኪያ ያለው ድስት ከበሮ ሊሆን ይችላል፤ ጥቅል ወረቀት እንደ ጥሩምባ ሊያገለግል ይችላል። እንዲሁም የተለያዩ ቁሳቁሶችን በመምታት መሞከርና መፈተን ይችላሉ፦ በእንጨት ሲመታ ምን ዓይነት ድምፆችን ያወጣል? በወለል ንጣፍ ላይስ? በብረት ላይስ? የሚወዱት ዘፈን ላይ ይወስኑና አንድ ላይ መጫወት ይችላሉ።
ሙዚቃ
ኦርኬስትራን መምራት
ማን ነው የሚመራው ማን ነች የምትመራው? – የሚወዱትን ሙዚቃ አንድ ላይ ሲያዳምጡ ትንሽ ዱላ በመያዝ ተጫዋቾቹን “መምራት” ይችላሉ። የሙዚቃው ድምጾች ላይ መደነስና የተለያዩ መሳሪያዎች ላይ መተወን፤ አልፎ አልፎም ሚናዎችን መቀያየር ይችላሉ።
ሙዚቃ