ትንሿ ዘማሪት ወፍ በጫካ ውስጥ ሁሉም የሚናገሩትን ለድብ መንገር እንዳለባት ይሰማታል። ነገር ግን ድቡ እርሷን ለመስማት አይቸኩልም። አንድ ደስ የሚል ነገር ልትነግረው ትፈልግ እንደሆነ ማወቁ ለእርሱ አስፈላጊ ይሆን? እውነት? ጠቃሚ ነው? በቀላልና በሚያስደስት ሁኔታ ድብ ዘማሪት ወፏንና እኛን የአሉባልታ ወሬዎችን ማስተላለፍ ዋጋ እንደሌለው ያስተምረናል። እንዲሁም በምትኩ መልካም ምክሩን ይሰጣል።
የእድሜ ክልል: ሁለተኛ ክፍል
ድንቢጥ በጫካ ውስጥ የሰማችውን አስደሳች ወሬ ለድብ ለመንገር በጣም ትጓጓለች። ድቡ ግን የትኞቹን ታሪኮች ማውራትና ማሰራጨት እንዳለባቸው ብሎም የትኞቹም ሳይነገሩ ቢቀሩ የሚል የራሱ የሆነ እይታ አለው። ድብ ድንቢጧንና እኛን አንባቢዎችን ሐሜተኛ ወሬና ጠቃሚ ታሪክን ለመለየት የሚረዳ ልዩ መስፈርት ያቀርባል።
“ምላስ መልካም ሲሆን ከእርሱ የሚበልጥ ነገር የለም”
(የዘሌዋውያን ሚድራሽ ራባ 33)
ማተሚያ ቤት:
מטר
የስርጭት ዓመት:
תשפ"ו 2025-2026

