דילוג לתוכן המרכזי בעמוד
የወሩ መጽሐፍ

ድመቱ ሻኡል


በ: ኤሪክ ሊትዊን ምሳሌዎች: ጀምስ ዲን

ድመቱ ሻኡል በነጭ ጫማው መራመድ ይወዳል። ነገር ግን እንጆሪ ክምር ውስጥ ቢገባ ምን ይሆናል? በሰማያዊ እንጆሪ ተራራ ላይስ? ሻኡል በዙሪያው ያለው እውነታ ሲቀየር እንኳን ሳይቀር ደስ ብሎት መዘመር ይችል ይሆን? - ስለ ቀለሞችና ያልተጠበቁ ነገሮችን ስለማስተናገድ የሚናገር አዎንታዊ ታሪክ።

የእድሜ ክልል: ታዳጊዎች

ድመቱ ሻኡል በደስታ ውስጥ ሆኖ በነጭ ጫማው ይራመዳል። በመንገድ ላይ ጫማው በአጋጣሚ በእንጆሪ ክምር፣ በሰማያዊ እንጆሪ ክምር፣ በኩሬ ጭቃና በውሃ ገንዳ ውስጥ ጠልቆ ይገባል። ጫማዎቹ ይቆሽሹና ቀለማቸው ይለወጣል፦ ደስ የማይል ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ሻኡል መልካሙን አይቶ በደስታ መንገዱን ይቀጥላል። ምክንያቱም ሕይወት ውብና በቀለማት የተሞላች ናትና።

በእርሱ ላይ ስለደረሰው ነገር ሁሉ እንዲህ ይል ነበር፦ ይህም ደግሞ ለበጎ ነው።
(በማሴኼት ታዓኒት 21 ገጽ ሀ መሰረት)

ታሪኩን ተከትሎ የሚመጣ ቪዲዮ

ማተሚያ ቤት:

כנרת

የስርጭት ዓመት:

תשפ״ה 2024-2025