דילוג לתוכן המרכזי בעמוד

አያት ያሽካ የባህር ዳርቻውን ያድናል


በ: ዮሲ አቡላፊያ ምሳሌዎች: ዮሲ አቡላፊያ

አያት ያሽካ በባህር ዳርቻ ላይ ይኖራል። ወፎችን ይፈልጋል፤ ፈጠራዎችን ይፈጥራል። የገንቢዎች ቡድን ወደ ባህር ዳርቻ ሲደርስ አያት ኢሽካና ልጆቹ ኡዲና ታማር ወራሪዎችን ለመዋጋትና በባህር ዳርቻ ላይ ፋብሪካ ወይም ሕንፃ እንዳይቋቋም ለመከላከል ኃይላቸውን ያስተባብራሉ። ግን ግንበኞች ያቀዱት ይህንን ነበር? አካባቢንና ተፈጥሮን የሚያከብር የደራሲና ሠዓሊ ዮሲ አቡላፊያ አዝናኝ ታሪክ።

የእድሜ ክልል: ሁለተኛ ክፍል

ትንሽ አለመግባባት ወደ ትልቅ ጀብድ ያመራል። በተንኮልና ሽኩቻ የተሞላና አንድ ግብ በሁሉም ሰው ዓይን ፊት ይቆማል – ተፈጥሮንና አካባቢን መጠበቅ። በዮሲ አቡላፊያ ልዩ መጽሃፍ ውስጥ በአያት ያሽካ አካባቢን የመንከባከብ ታላቅ ፍቅር እንዲለከፉ የተጋበዙ ሲሆን በልዩ ፈጠራዎቹ በኡዲና ታማር ጥበብ ተነሳሽነት በሕይወት ውስጥ ነገሮች ሁል ጊዜ በመጀመሪያ እይታ እንደሚመሥሉ እንዳልሆኑ ይማሩ።
ዓለሜን እንዳታበላሽና እንዳታጠፋ እርግጠኛ ሁን
(መክብብ ራባ 7፡13)

ዮሲ አቡላፊያ ሥዕላዊ፣ ካርቱኒስት፣ አኒሜተርና የሕፃናት መጻሕፍት ጸሐፊ ​​ነው። በስራዎቹ ብዙ ሽልማቶችን አሸንፏል። አቡላፊያ አብዛኞቹን የሜኢር ሻሌቭ መጽሃፍትን ሥዕል ስሏል። የእርሱ ምሥሎች በዝርዝር የበለፀጉና ቀላል ሲሆኑ ፈገግ ያሉ ለሰውና ተፈጥሮ ፍቅርን የሚያንፀባርቁ ናቸው።

ታሪኩን ተከትሎ የሚመጣ ቪዲዮ

ማተሚያ ቤት:

עם עובד

የስርጭት ዓመት:

תשפ״ה 2024-2025