דילוג לתוכן המרכזי בעמוד

ከእግር ጣት እስከ ጭንቅላት ድረስ


በ: ኤሪክ ካርል • ምሳሌዎች: ኤሪክ ካርል

ማን እንደ ዝሆን ሊረግጥ ይችላል? አንገትን እንደ ፔንግዊን ማዞርስ? በእጅ እንደ ባህር ውሻ ማጨበጨብስ? በመጽሐፉ ውስጥ ያሉት እያንዳንዱ እንስሳት የተለየ እንቅስቃሴ ያስተምሩናል። ወላጆችና ታዳጊዎችም እንዲሞክሩትና እንዲያደርጉት ይጋብዛሉ።

የእድሜ ክልል: ጨቅላ ህፃናት

ከታዳጊ ልጆች ጋር ማንበብ

ስለ መጽሐፉ

ታዳጊዎች በፍጥነት ያድጋሉና ብሥለትንም ይጨምራሉ። በየቀኑ በመመልከት፣ በማስመሰልና በመሞከር አዳዲስ እውቀቶችንና አካላዊ ክህሎቶችን ያገኛሉ። በኤሪክ ካረል (‘የተራበው አባጨጓሬ’) የተፃፈውና የተገለፀው መፅሃፍ ታዳጊ ህፃናትን ከተለያዩ እንስሳት ጋር ያስተዋውቃቸዋል። በእነሱም እርዳታ የሰውነታቸውን ብዙ የመንቀሳቀስ እድሎችን ማጤን ይችላሉ።

ታሪኩን ተከትሎ የሚመጣ ቪዲዮ

ማተሚያ ቤት:

מודן

የስርጭት ዓመት:

תשפ"ו 2025-2026