"ቅጠሉ በመላው ዛፍ ላይ በጣም ቡናማ ስለነበረ ሻልኬቱም አስደናቂ ስሜት ተሰምቶታል።" ለሻልኬቱ በዛፉ ላይ የእርሡ ብቻ የሆነ አንድ ቅጠል ያለው ሲሆን እርሡንም ያስደስተዋል። ቅጠሉ ቀለም ሲቀያይር፣ ሲደርቅ አልፎ ተርፎም በነፋስ ሐይል ሲረግፍ ሻልኬቱ የሙሉ ኩባያውን ግማሽ ማየቱን በመቀጠል በመንገዱ ላይ ስለ ብሩህ ተስፋ መሠነቅንና መልካሙን ማየትን ያስተምረናል።
የእድሜ ክልል: መዋዕለ ሕጻናት
ሻልኬት ቅጠሉን እያሳደገ እያለ እስኪረግፍ ድረስ ቅጠሉ መልኩን ሲቀይር ይመለከታል። በእያንዳንዱ ለውጥ አስደናቂ ስሜት ይሰማዋል። ልክ እንደ ተፈጥሮ በሕይወት ውስጥ ዑደት አለ፦ ከዓመት እስከ ዓመት፣ ከልጅነት እስከ እርጅና። መርገፍ የመጨረስና የመሰናበቻ ምልክት ቢሆንም የመታደስም ምልክት ጭምር ነው። ሃሻልኬት የሕይወት ለውጦችን እንድንቀበል፣ ለመውደድና ለመተው እንድንስማማ፣ መልካሙን እንድናይና እንድንመለከት የሚጠቁም የፍልስፍና መጽሐፍ ነው።
ሁሉን በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው
(መክብብ 3፡11)
ለትንንሾችና ለአዋቂዎች ፍልስፍና
የፍልስፍና ቃና ያላቸው የህፃናት መጽሃፎች አንባቢዎች መጽሐፉን እንደ እድሜያቸው በተለያየ ደረጃ እንዲገናኙ ያስችላቸዋል። በሻልኬት ገጸ ባህርይ በኩል ስለ ዓለማችን እይታና ለውጦችን ለመቋቋም ስለምንፈልገው መንገድ ጥያቄዎችን መጠየቅ እንችላለን።
ታሪኩን ተከትሎ የሚመጣ ቪዲዮ
גדלים עם ספריית פיג’מה!
ማተሚያ ቤት:
ספרית פועלים
የስርጭት ዓመት:
תשפ"ו 2025-2026