ከመኝታ በፊት ባሉት ጥቂት ጊዜያት ወንድምና እሕት እርስ በርሳቸው ይነጋገራሉ። "እኔ ትልቅ ነኝ" ይላል ወንድም። "እኔ እበልጥሃለሁ" ትላለች እሕት። እንደ ፉክክር የተጀመረው ወደ መለያነት እያደገ ይሄድና በመጨረሻም ወደ ማራኪ የፍቅር መግለጫነት ይቀየራል።
የእድሜ ክልል: ቅድመ ትምህርት ቤት
ውድድርና ንጽጽር የሴትና ወንድ ልጆች እድገት ዋነኛ አካል ናቸው። በማሕበራዊ ክህሎቶችና በግል እድገት ውስጥም ትልቅ ሚና ይጫወታሉ። በታሪኩ ውስጥ ያሉት ወንድማማቾች እርስ በእርሳቸው ቢፎካከሩም አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ እርስ በርስ ይደጋገፋሉ። መጽሐፉ በአስተማማኝና በፍቅር ግንኙነት ላይ የተመሰረተ አጫዋች ፉክክርን እንድንለይ ይጋብዘናል።
“ጓደኛ ሁነኝ፣ ወንድም ሁነኝ፣ ስጠራህ ድረስልኝ”
(“ጓደኛሁነኝ፣ ወንድም ሁነኝ”) ከሚለው የዮራም ታሃርሌቭ ሥንኝ የተወሰደ)
ማተሚያ ቤት:
זברה
የስርጭት ዓመት:
תשפ"ו 2025-2026