משל
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ውይይት - ሸምበቆ ወይስ ዝግባ?
በሕይወት ውስጥ ስለ መቀያየርና መቋቋም ማውራት እንችላለን። እንደ ዝግባ ባለንበት ከአቋማችን ለመንቀሳቀስ ዝግጁ ባልሆንባቸው ሁኔታዎችና ተለዋዋጭ በሆንባቸው ባህርያችንን ወይም አስተሳሰባችንንም በምንቀይርባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ከዕለት ተዕለት ሕይወት ምሳሌዎችን ማጋራት ጠቃሚ ነው – ፍላጎቶቻችን እንደጠበቅናቸው መሟላት ሳይችሉ ሲቀር ምን ይከሰታል?
ሸምበቆውና ዝግባው
ታሪክ ይስሙ
የመጽሐፉ ማጀቢያ የQR ኮዱን ስካን በማድረግ ይጠብቅዎታል በማንኛውም ጊዜ ዘና ማለትና ታሪኩን አብረው ማዳመጥ ይችላሉ። እንዲሁም ለአዲስ ገቢ ቤተሰቦች ተስማሚ ነው።
ሸምበቆውና ዝግባው
ሰውነትን የማቀያየር መልመጃ
ጉልበቶችዎ እርስ በእርሳቸው እንዲተያዩ ሆነው መቀመጥ። ወደ ውስጥ መተንፈስና እጆቻችሁ ከላይ እስኪደርሱ ድረስ ወደ ሰውነታችሁ ጎን ማንሳት። ከዚያም እጆችዎን ወደ ፊት በሚያወርዱበት ጊዜ አየሩን ወደ ውጪ ማስወጣት። በእያንዳንዱ ጊዜ ትንሽ ልምምድ እያደረጉና ተጨማሪ ልምምዶችን ማድረግ ይኖርብዎታል። ለጤና ያድርግልዎት!
ሸምበቆውና ዝግባው
የሸምበቆ-ዝግባ ጨዋታ
የሸምበቆ ተቃራኒው ምንድን ነው? – ዝግባ! የሙቀትስ ተቃራኒው ምንድነው? – ቀዝቃዛ! የአሮጌስ ተቃራኒ? ተለዋዋጭ? የተረጋጋ? ኮምጣጣ? ሕፃን? – እያንዳንዱ ተሳታፊ በተራው አንድ ቃል ይናገራል፤ የተቀሩት ደግሞ የተቃራኒውን ቃል ማግኘት አለባቸው። የ… ተቃራኒስ ተቃራኒው ምንድን ነው?
ሸምበቆውና ዝግባው
ሸምበቆውና ዝግባው