דילוג לתוכן המרכזי בעמוד

እባካችሁ መሃል ላይ ልሆን እችላለሁ?


በ: ሱዛን ስትራዘር • ምሳሌዎች: ሱዛን ስትራዘር

ሁሉም ሰው ታሪክ መሥማት ይፈልጋል። ግን ሁሉም የራሡ ፍላጎት እያለው እንዴት ማንበብን ማስጀመር ይችላሉ? አንዱ ምቹ ትራስ ይፈልጋል፤ ሌላኛው መሀል ላይ መቀመጥ ይፈልጋል። ጓደኛን ለመጠበቅ አጥብቀው የሚሹም አሉ። ደስተኛ የሆነው ቡድንስ ታሪክ መስማት ይችል ይሆን? መልሱ በስተመጨረሻው ብቻ የተገለጠ ጣፋጭ ታሪክ ከአስቂኝ ምሥሎች ጋር።

የእድሜ ክልል: ቅድመ ትምህርት ቤት

ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-

ልጁ አንድ ታሪክ ሲጠቁም – ሁሉም ሰው ፍላጎት አለው! ነገር ግን ንባቡ ደጋግሞ ዘግይቷል። ምክንያቱም በእያንዳንዱ ጊዜ ከጓደኞቹ አንዱ የተለየ ነገር ያስፈልገውና ሌሎች ደግሞ እርሱን ግምት ውስጥ በማስገባት ራሣቸውን ለማስማማት ይሞክራሉ። አውራሪሱ ሲመጣ ሁሉንም ነገር ይገለባብጣል። እርሱ የፈጠረው ውጥንቅጥ ቢሆንም አውራሪሱ በቡድን ውስጥ በፍቅር ተቀባይነትን አግኝቷል። ይህም በተባበረ ቡድን ውስጥ ለሁሉም ሰው የሚሆን ቦታ እንዳለ ያስተምረናል።

“ወንድሞች በአንድነት ቢቀመጡ እነሆ መልካም ነው፤ ያማረም ነው”
(መዝሙረ ዳዊት 133:1)

ታሪኩን ተከትሎ የሚመጣ ቪዲዮ

ማተሚያ ቤት:

תכלת

የስርጭት ዓመት:

תשפ"ו 2025-2026