סִפְרֵי הַחֹדֶשׁ
ሐኑካ ሊመጣ ትንሽ ነው የቀረው። ስለዚህ ይላጣል፣ ይቆረጣል፣ ይነሳሳል፣ ይጠበሳል! - በቀላል ቋንቋና በምት የታጀቡ ዜማዎች ለሐኑካ የሚሆን የቤተሰብ ፓንኬኮች ዝግጅት ተገልጿል!
הוצאה: ספרית פועלים
በዝናብ ውስጥ መራመድ እንዴት አስደሳች ነው፤ ዣንጥላ የሌለው ሰው ግን ምን ያደርጋል? - የታወቀውና የተወደደው የልጆች ዘፈን ዣንጥላ ስላላት አንዲት ልጅ ይተርካል። እርሷን እንዲቀላቀል የሚፈልግን ሁሉ እየጋበዘች አብሮ ጉዞ ማድረግ ምን ያክል የበለጠ አስደሳች እንደሆነ ትገልጣለች።
הוצאה: מודן
חודש חלוקה: (פברואר/שבט)
ሳቁ የት ነው የሚደበቀው? በእጆች ውስጥ? በእግሮች ውስጥ? ጀርባ ላይ? ምናልባትም በባህር መሃል ላይ ሊሆን ይችላል? - አያ ሳቅን ትፈልጋለች፤ ሳቅ በውስጧ እንዳለ እስክታውቅ ድረስም እግረ መንገዷን የአካል ክፍሎችን ትተዋወቃለች፤ እንዴት ድንቅ ነው!
ቲም ታም ወጣት ጥንዚዛ ስትሆን እስካሁን የራሷ የሆነ ነቁጥ የላትም። ነቁጦችን ለመፈለግ ከእናቷ ጋር ትወጣና በእያንዳንዱ ነጥብ ባገኘችው መጠን እያደገችና ትንሽ የበለጠ ነፃ እየሆነች ትሄዳለች። ልጆች ቀጣዩን ነጥብ ራሳቸው እንዲፈልጉ በሚጋብዙ ጥበባዊ ሥዕላዊ መግለጫዎች የታጀበ ስለ ማደግና ስለ ነፃነት የሚያሳይ አዲስ መጽሐፍ።
הוצאה: עם עובד
አንድ ልጅ ውሻ ይፈልጋል። ግን ድመትን በስጦታ ይቀበላል። ድመቷ እንደ ውሻ አይጮኽም፣ ሲታዘዝ አይቀመጥም፣ ኳስ አያመጣም። ምክንያቱም ድመት ውሻ አይደለም። ግን ... ያም ሆኖ ምናልባት ከልጁ ጋር ሊስማማ ይችል ይሆን? ስለ ተስፋዎች፣ ብስጭቶችና አንዳንድ ጊዜ በትክክል ያልፈለግነው ነገር ለእኛ ምርጥ ነገር ሆኖ እንዴት እንደሚሆን የሚናገር አስደሳች ታሪክ።
הוצאה: הקיבוץ המאוחד
እናት ኢያሱን ከዶሮው ቤት እንቁላል እንዲያመጣ ትልከዋለች፤ ግን ውይ እንቁላሉ ተሰበረ! ኢያሱና እናቱ ተስፋ አይቆርጡም። በየቀኑ ኢያሱ ወደ ተግባር እየቀረበ ስለ ዓለምና እንዴት አንድ ሙሉ እንቁላል ወደ ቤት እንዴት ማምጣት እንደሚችሉ ትንሽ ተጨማሪ ይማራሉ። ስለ እምነትና ስለ ነፃነት የሚገልጽ በአስቂኝ ዘይቤ በሚገርም ምሳሌዎች የታጀበ ግጥም ታሪክ።
הוצאה: אגם
ድመቱ ሻኡል በነጭ ጫማው መራመድ ይወዳል። ነገር ግን እንጆሪ ክምር ውስጥ ቢገባ ምን ይሆናል? በሰማያዊ እንጆሪ ተራራ ላይስ? ሻኡል በዙሪያው ያለው እውነታ ሲቀየር እንኳን ሳይቀር ደስ ብሎት መዘመር ይችል ይሆን? - ስለ ቀለሞችና ያልተጠበቁ ነገሮችን ስለማስተናገድ የሚናገር አዎንታዊ ታሪክ።
הוצאה: כנרת
"እዚያ በጸጥታ የሚራመደው ማነው? ጥንዚዛ! ያለ ጥድፊያ የሚሳበው? ቀንድ አውጣ!" - ልጅቷ አየሌት ለጉዞ በመውጣት ከወጣት አንባቢዎች ጋር አንድ ላይ አስገራሚ እንስሳ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ታገኛለች። አየሌት ማንንም ወደ ኋላ አትተውም፤ እንደ ጉዞ አጋሮች በማድረግ ብሎም በቤት ውስጥ እንግዶች በማድረግ ለእያንዳንዱ እንስሳ ቦታ ታገኛለች።
הוצאה: כנרת זמורה
יש להזין את הקוד שנשלח כדי להיכנס
להאזנה לחצו