סִפְרֵי הַחֹדֶשׁ
በድቡ የአትክልት ቦታ ውስጥ አዲስ ተክል ይበቅላል። ነገር ግን ለማበብ ፈቃደኛ አልሆነም። ድቡ ለመርዳት ይሞክራል፤ ግን እስከዚያ ድረስ ከመሬት በታች ምን እየሆነ ነው? አዝናኝ ምሳሌዎቹ አንዳንድ ጊዜ የምስሉን ክፍል እንደምናየው ብቻ የሚያሳዩ ሳይሆኑ ትይዩና አስገራሚ ክስተቶችን ያስቃኛሉ።
הוצאה: מטר
ማታን ወደ አራት ዓመቱ ነው። እራሱን ችሎ ሲለብስ ትልቅ ስሜት ይሰማዋል። ነገር ግን በአጋጣሚ ሳህን ሲሰብር ትንሽ እንደሆነ ይነግሩታል። እንዴት ግራ እንደሚያጋባ። ማታን ትንሽ ወይም ትልቅ መሆኑን እንዴት ያውቃል? ምናልባትም እርሱ ሁለቱንም ሊሆን ይችላል? ማታን በዚህ እድሜ ውስጥ ያሉ የብዙ ህጻናት ድብልቅ ስሜቶችን በለስላሳና በሚማርክ መልኩ ይገልጻል።
הוצאה: מאגנס
ክሬመር የድመቷ ጓደኞቹ ከእርሱ ጋር የድመት ጨዋታዎችን ለመጫወት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እርሱ በመቧጨርና በመናከስ ምላሽ እየሰጠ ወደ ጫካው ይሸሻል። በጨለመው ጫካ ውስጥ ማንን ይገናኝ ይሆን? ማንስ ሊረዳው ይችል ይሆን? በሜኢር ሻልቭ ተወዳጅ ክላሲክ።
הוצאה: עם עובד
ከሁሉም ሰው ጋር ስለሚጣላ ልጅ፦ ከልጆች፣ ከእንስሳትና ከእቃዎች ጋር እንኳን ሳይቀር። አንድ ቀን ከመጥረጊያ ጋር መጣላት ጀመረ፤ ይሄንን ተአምር እዩ እስኪ - መጥረጊያው ምላሽ ይሰጣል፤ ግዳጅ ውስጥ ሳይገባ ይቀራል! ታሪኩ በቀላልና በሚያዝናና መልክ በጸብ ጊዜ የልጆችን ስሜት በመግለጽ ምንም እንኳን ሁሉንም ነገር ሁል ጊዜ ማስተካከል እንደሚቻል ያስታውሰናል።
הוצאה: המבוך
"ምን እናድርግ? ከዚህ እንዴት እንቀጥላለን? እንዴት እናውቃለን እንዴት እናውቃለን አፊኮማኑ ወዴት ነው?" ግጥሙንና ምቱን በጠበቀ ታሪክ ሁሉም የቤቱ አባላት የጠፋውን አፊኮማን ይፈልጋሉ። የት እንደጠፋ ማን ያውቅ ይሆን? ማንስ ያገኘው ይሆን? ጣፋጭ ታሪክ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ የፋሲካ ወግና በዝግጅቱ ላይ የሚሳተፈው ለጋው ትውልድ እስኪተኛ ድረስ።
הוצאה: קוראים
ልጆቹ ይሳለቁበታል፤ አባት ይፈራል፤ አያት ትጠራጠራለች። ትንሿ ኤፍራት ግን በእምነት ተሞልታለች። የውጪ ድምፆች በራስ የመተማመን ስሜቷን እንዲያናውጡ አትፈቅድም። ያገኘችውን ትንሽ ጫጩትም ክንፏን ዘርግቶ ለመብረር እስኪችል ድረስ መንከባከቧን ትቀጥላለች። ታላቅ ስራ ስለምትሰራ ትንሽ ልጅ ታሪክ።
הוצאה: כנרת
ጠርሙስ የሌለበት ቡሽ፣ አሮጌ ቱቦዎችና በባህር ዳርቻ ላይ የተጣለ ማበጠሪያ እንኳን ሳይቀር - እነዚህ ሁሉ በትክክለኛው ዓይኖች ከተመለከቷቸው ትልቅ ጨዋታና ፈጠራ ሊሆኑ ይችላሉ። በታሪኩ ውስጥ ላለው ልጅ ምንም ነገር "እንዲሁ" አይደለም። ማንኛውም ነገር ተአምር ሊሆን ይችላል፦ የሚያገኛቸው የተለያዩ ነባራዊ ሁኔታዎችና እንዲሁም የባህር ላይ ጉዞ።
יש להזין את הקוד שנשלח כדי להיכנס
הורים יקרים וצוותים חינוכיים, אתר ספריית פיג’מה החדש לרשותכם, עם תכנים מעניינים ומעשירים ילדים/ות.
באתר תוכלו למצוא המון פעילויות שתוכלו לעשות יחד, סרטונים וספרים להאזנה שיעזרו להעברת הזמן עם הילדים בימים קשים אלה.
למעבר לפעילויות