אֲנִי וְעַצְמִי
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
በአንድ ወቅት ብቻውን መተኛት የማይፈልግ ልጅ ነበር
ድራማ – ታሪክ ከአሻንጉሊቶች ጋር
የልጆችዎ ተወዳጅ ፀጉር አሻንጉሊቶችና የእንስሳት መጫወቻዎች እንዲሁ የታሪኩ አካል ሊሆኑ ይችላሉ፦ በእያንዳንዱ ጊዜ የተለየ አሻንጉሊት እየጨመሩና እየቀነሱ ታሪኩን አንድ ላይ ይተውኑ።
በአንድ ወቅት ብቻውን መተኛት የማይፈልግ ልጅ ነበር
ጨዋታ - በብርድ ልብስ ውስጥ ማን ይተኛል?
ታዳጊው ሕጻን ዓይኖቹን ይዘጋና አሻንጉሊቷን እርስዎ ከብርድ ልብስ በታች ይደብቃሉ። ዓይኖቹን ሲከፍት እርስዎ ወላጆች ስለ እንስሳው ማንነት ፍንጭ ይሰጣሉ፤ ታዳጊው መገመት አለበት። ይጮኻል? ምናልባትም ይዘላል ካሮትስ ይበላል? ሚናዎችን መቀያየርና ታዳጊው እርስዎ በብርድ ልብስ ስር የደበቁትን ማን እንደሆነ እንዲጠቁማችሁ መፍቀድ ይችላሉ?
በአንድ ወቅት ብቻውን መተኛት የማይፈልግ ልጅ ነበር
በአንድ ወቅት ብቻውን መተኛት የማይፈልግ ልጅ ነበር
ለቤተሰባዊ ንባብ ጠቃሚ ምክር
ታዳጊ ሕጻናት “በስዕላዊ መግለጫዎች ውስጥ ያነባሉ”። ስዕላዊ መግለጫዎችን መመልከት ለዝርዝሮች ትኩረት እንዲሰጡና ለሥነ ጥበብ እንዲጋለጡ ያስተምራቸዋል። ከስዕላዊ መግለጫው ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን አልፎ አልፎ መጠየቅ ትችላላችሁ፤ ለምሳሌ፦ ዝንቡ የት አለ? እስስቷ ምን እያደረገች ነው?
እንዴት መወሰን እንዳለባት የማታውቀው እስስት
በቀለማት ማንበብ
በሚያነቡበት ጊዜ በቃላቱና በስዕሉ ላይ የሚታየውን ዋናውን ቀለም ለታዳጊ ህፃናቱ ማመልከት ይችላሉ። ታዳጊው ሕጻን የቀለም ስም ገና ባያውቅም እንኳ በቀለማት ያሸበረቁ ስዕላዊ መግለጫዎችን በመመልከት ይደሰታል።
እንዴት መወሰን እንዳለባት የማታውቀው እስስት
ፈጠራ - ቀለማትን የምትቀያይር እስስት
ቀለማትን የምትቀያይር እስስት ይፈልጋሉ? – ኮዱን ስካን ያድርጉና የእስስቷን ሥዕል በተንሸራታች ላይ ፕሪንት በማድረግ እንዴት ባለ ቀለም ሊንጠባጠብና አልፎ ተርፎም ሊካተት እንደሚችል ይወቁ።
እንዴት መወሰን እንዳለባት የማታውቀው እስስት
ነገሮች በቀለማት መሰረት
ቀይ ኳስ አላችሁ? በቤታችሁ ውስጥስ ቀይ ሌላ ምን አለ? – አንድን ቀለም ማስታወቅና በተመረጠው ቀለም ውስጥ እቃዎችን ለመሰብሰብ አንድ ላይ መውጣት ትችላላችሁ፦ ዝኩኒ፣ የተከተፈ ተክልና ሌላ ምን አረንጓዴ ነገር ማግኘት ትችላላችሁ?
እንዴት መወሰን እንዳለባት የማታውቀው እስስት
ጨዋታ - እኔ እንደ ማን ነኝ?
“በአራቱም እግሮቼ እየተሳበኩ ቀለሜን እቀያይራለሁ እንደ… እስስት!” በእያንዳንዱ ዙር እንስሳ ላይ ይወሰናል፤ ወላጆች ያሳዩና ታዳጊው ሕጻን ይቀላቀላል፦ “እኛ አንበሶች ነን – ኑ እናግሳ!” “እኛ ቡችላዎች ነን – ኑ እንጩኽና ጅራታችንንም እናወዛውዝ!”
እንዴት መወሰን እንዳለባት የማታውቀው እስስት
እንዴት መወሰን እንዳለባት የማታውቀው እስስት
ግጥሞችን ማንበብ
በመጽሐፉ ውስጥ ያሉት ግጥሞች ትንሽ የሕይወት ጊዜዎችን ያቀርባሉ። በእያንዳንዱ የጋራ ንባብ ውስጥ ሌላ ዘፈን በመምረጥ አንድ ላይ ማንበብ አለብዎት። ዘፈኑ በእርስዎ ላይ የደረሰን ነገር ያስታውሳል? ይህ ለእናንተ፣ ለወላጆች ከልጅነታችሁ ጀምሮ ልምዶቻችሁን እንድትካፈሉና በዚህም ከልጅነትና ከልጆች ጋር መቀራረብንና መጋራትን የምትፈጥሩበት እድል ነው።
ለምን ሁሌም ያስታውሱኛል
ከሐጊት ቤንዚማን ጋር መተዋወቅ
ደራሲ ሐጊት ቤንዚማን መቼ መጻፍ ጀመረች? እርሷ ስለ ምን ትጽፋለች ለምንስ? – የQR ኮዱን ስካን ካደረጉ ፈጣሪዋንና ስራዋን መተዋወቅ ይችላሉ።
ለምን ሁሌም ያስታውሱኛል
የቤተሰብን አልበም መመልከት
የወላጆችን የፎቶ አልበሞች አንድ ላይ በማየት ከልጅነት ጀምሮ ልዩ ጊዜዎችን መፈለግ ጥሩ ሀሳብ ነው። እንዲሁም የልጅነትና የልጆች ቀደምት ፎቶግራፎችን ማየትና የተቀረጹበትን አፍታዎች ማጋራት ይችላሉ። በእናንተ ውስጥ ምን ትዝታ ያስነሳሉ?
ለምን ሁሌም ያስታውሱኛል
አንድ ላይ ድራማ መስራት
איזה שיר אהבתם במיוחד? – תוכלו להציג אותו יחד, כשהמבוגרים מציגים את תפקיד הילדים, ולהפך.
ለምን ሁሌም ያስታውሱኛል
ለምን ሁሌም ያስታውሱኛል
ውይይት - ስሜ
ይቅርታ ስምህ ማን ነው? – ስለ ስሞቻችሁ ማውራት ትችላላችሁ – እናንተ ወላጆች በስማችሁ የተጠራችሁት ለምንድነው? ለወንድና ለሴት ልጆችስ የሚጠሩበትን ስም ለምን መረጣችሁ? ቅፅል ስሞች አላችሁ? እንዴት አገኛችኋቸው?
ስሜ ዮዮ ይባላል
ዮዮን በመከተል መንቀሳቀስ
ዮዮ ይዘላል፣ ይቀመጣል፣ ይወጣል… በእያንዳንዱ ሥዕል ዮዮ በተለየ ቦታ ላይ ይታያል። ዮዮን መተወን የምትችሉ ሲሆን የተቀረው ቤተሰብ እናንተ ባቀረባችሁበት መንገድ ዮዮ በመፅሃፉ ላይ የት እንደሚገኝ ይፈልጋል። ተሳካላችሁ? – ወደ ቀጣዩ ተሳታፊ ትወና መሄድ ይቻላል።
ስሜ ዮዮ ይባላል
እኔ ሁሌም እኔ ሆኜ እቆያለሁ - ዳቲያ ቤን-ዶር
አንዳንድ ጊዜ ትደሰታላችሁና አንዳንድ ጊዜ ታዝናላችሁ? – የመጽሐፉ ደራሲዋ ዳቲያ ቤን-ዶር የልጆቹን “እኔ ሁሌም እኔ ሆኜ እቀራለሁ” የሚለውን ዘፈን የጻፈች ሲሆን ዑዚ ሂትማን አቀናብሮታል። የQR ኮዱን ስካን ማድረግና ዘፈኑን መቀላቀል ይችላሉ!
ስሜ ዮዮ ይባላል
የፈጠራ ስራ - የ"እዚህ በጥሩ ሁኔታ ይኖራሉ" ታፔላ
የፈጠራ ቁሳቁሶችን ያዘጋጁ፦ የካርቶን አራት ማዕዘን፣ ቀለሞች፣ ማጣበቂያዎችና ምናልባትም ፕላስቲሲን ይቻላል።
ይጻፉና ያስጊጡ፦ በታፔላው መሃል ላይ ስምዎን በመጻፍ፣ በመሳልና በማስጌጥ በክፍሉ መግቢያ ላይ ለመስቀል ጊዜው አሁን ነው!
ሌላ ሀሳብ – የእርስዎን ፎቶዎች ፕሪንት በማድረግ በታፔላው ላይ መለጠፍና ስሞቹን መጻፍ ይችላሉ [ምን እንደ ተባለ ግልጽ አይደለም – የእርስዎ ገጸ ባህርያት]
ስሜ ዮዮ ይባላል
ስለ ፍርሃትና ማበረታታት መወያየት
የሴቶችና ወንዶች ልጆች እድገት ሂደት በተለያዩ ፍርሃቶች የታጀበ ነው። ስለእነርሱ ማውራት እነርሱን ለመቋቋምና የመተማመን ስሜትን ለመፍጠር ይረዳል። ስለ ፍርሃቶች አብረው መወያየት ይችላሉ፦ የሚያስፈራው ምንድን ነው? ለማሸነፍ የሚረዳውስ ምንድን ነው?
እስከ ላይ
እስከ ላይ
በመጫወቻ ስፍራው ውስጥ
ታሪኩን ተመርኩዘው ወደ መጫወቻ ቦታዎች አብረው በመሄድ የተለያዩ መገልገያዎችን በጋራና በተናጠል መሞከር ይችላሉ። እንዲሁም በመገልገያዎች መካከል የሚሄድ ለሁሉም ተሳታፊዎች አስደሳች የሆነ መንገድም ሊያመጡ ይችላሉ።
እስከ ላይ
ቤተሰባዊ ማበረታቻ
ማዕያን ስትፈራ ሁሉም “አይዞሽ ማዕያን!” ይሏታል። እናንተስ እንዴት እርስ በርሳችሁ መበረታታት ትችላላችሁ? በቤተሰብ የማበረታቻ ቃላት ላይ መወሰን፣ ምናልባትም የሚያበረታታ ዘፈን ማግኘት ወይም ደስታንና ጉልበትን የሚሰጣችሁን ንባብ በጋራ ማንበብ ይቻላል።
እስከ ላይ
עַכְשָׁו בָּפּוֹדְקַאסְט שֶׁל סִפְרִיַּת פִּיגָ'מָה!
הַסִּפּוּר לְהַאֲזָנָה – עַכְשָׁו בָּפּוֹדְקַאסְט שֶׁל סִפְרִיַּת פִּיגָ’מָה!
עידוד קריאה משפחתית – כדאי לספר למשפחות שהגיע ספר העוסק בַּכוח ובעידוד שאנחנו שואבים מהמשפחה. הספר מלווה בפסקול להאזנה משפחתית משותפת. הפסקול מתאים גם למשפחות עולים.
እስከ ላይ
ፍለጋንና ማግኘትን አስመልክቶ የሚደረግ ውይይት
መጽሐፉን ተከትሎ ከወላጆች፣ ከወንድ አያት፣ ከሴት አያት ወይም ከሌሎች ዘመዶች ጋር በመሆን የፍለጋ ጉዞ ማድረግ ትችላላችሁ፦ ምን አገኛችሁ? ተገረማችሁ? መፈለግና ማግኘት ትወዳላችሁ?
እኔ መፈለግ እወዳለሁ
ጨዋታ - የኳ-ኳ ፍለጋዎች
ለሚፈልጉና ለሚያገኙ የሚሆን የጋራ ጨዋታ!
የQR ኮዱን ስካን ያድርጉ
በመመሪያዎቹ መሰረት ፕሪንት ያድርጉ፣ ይቁረጡና ይጠፉ።
ፈለጉ? አገኙ? እንደገና መጫወት ይፈልጋሉ?
እኔ መፈለግ እወዳለሁ
ስዕላዊ መግለጫዎች
በመጽሐፉ ውስጥ በቀለማት ያሸበረቁና ጥቁርና ነጭ የሆኑ ስዕላዊ መግለጫዎች ይገኛሉ –
ስዕሎቹ በጥቁርና ነጭ ሲሆኑ እና ስዕሎቹ በቀለም ያሸበረቁ ሲሆኑ መከታተልና መለየት ይችላሉ?
እኔ መፈለግ እወዳለሁ
ጨዋታ - የጠፋው ምንድን ነው?
ብዙ እቃዎችን በተከታታይ ያስቀምጡና በጥንቃቄ ይመልከቱ።
በእያንዳንዱ ጊዜ የቤተሰቡ አባላት ዓይኖቻቸውን ይዘጉና ከቤተሰብ አባላት አንዱ አንዱን እቃ ይደብቃል።
ከዚያ በኋላ ዓይኖቻቸውን ከፍተው ይፈልጋሉ – የትኛው እቃ ጠፋ? የት ነው የደበቁት?
እኔ መፈለግ እወዳለሁ
በጣም ደስ ይላል - ኢላኒት!
እኔ እንቁራሪት እመስላለሁ ነገር ግን በጣም ትንሽ ነኝ፤
የምኖረው በእስራኤል ነው፣ በዋናነት በዛፎች ላይ፣ የምበላው ነፍሳትን ሲሆን በውሃ ውስጥ እንቁላል እጥላለሁ።
ዛሬ እኔ ጥበቃ የሚደረግልኝ እንስሳ ነኝ ስለዚህም እኔ በተፈጥሮ ብቻ እንጂ በማሰሮ ውስጥ አላድግም።
እኔ መፈለግ እወዳለሁ
አብሮ ማንበብ
እያነበቡ ሳለ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ እጆችን ማካተት፣ መንገዳቸውን መከተል እና እንቅስቃሴያቸውን በማስመሰል ጠቃሚ ነው። ወላጆች እና ታዳጊዎች ባንድነት ሆነው ይህንን ማድረግ ይችላሉ፦ እጅን በጣት ጫፍ ላይ “ያራምዱ”፣ እጅ እንዲዘል ያድርጉ፣ በሥዕሉ ላይ ያለውን በር ያንኳኩ እና የመጽሐፉን አጠቃላይ ንቁ አንባቢ ይሁኑ።
ስለ እጅ የሚገልፀው መጽሐፍ
የእጅ ጨዋታዎች
በእጅ መጫወት በጣም አስደሳች ነው! እያንዳንዱ ሰው በተራው አንድ የተወሰነ እንቅስቃሴ ያደርጋል፣ የተቀሩት ተሳታፊዎች ደግሞ ይኮርጃሉ። እጆችዎን ማጨብጨብ፣ ሰላም ወይም ደህና ሁኑ ብለው ማወዛወዝ፣ ለ “ዝምታ” ምልክት ማሳየት ወይም መብረር ይችላሉ!
ስለ እጅ የሚገልፀው መጽሐፍ
የእጆች ቤተሰብ
ትንሽ እጅ ያለው ማነው? ትልቅ እጅ ያለው ማነው? እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል እጁን በወረቀት ላይ እንዲያስቀምጥ ይጋበዛል። እርስዎ፣ ወላጅ፣ የእጆችን ቅርጽ ይሳሉ፣ እና ታዳጊዎች ያጌጣሉ እናም ይሳያሉ። የሁሉም እጆች ምስል እንደ ማስታወሻ ሊቀመጥ ይችላል፣ እናም እንቅስቃሴውን ከአመት አመት መድገም እና ምን እንደተለወጠ ማየት ይችላሉ።
ስለ እጅ የሚገልፀው መጽሐፍ
የሚዘምሩ እጆች
እንደ “አስር ጣቶች አሉኝ (I have ten fingers)” ወይም “ኮፍያዬ ሶስት ማዕዘን አለው (My hat has three corners)” በመሳሰሉት የእጅ እንቅስቃሴዎች የታጀቡ መዝሙሮችን መዘመር ይችላሉ። ወደ መዝሙርዎ የእጅ ምልክቶችን ማከል ጥሩ ሀሳብ ነው፣ እናም በሌሎች ተወዳጅ መዝሙሮች ላይ የጣት እንቅስቃሴዎችን ማከል ይችላሉ። ይዝናኑ!
“עשר אצבעות לי יש” מאת רבקה דוידית
מחרוזת שירי ידיים מאת דתיה בן דור
ስለ እጅ የሚገልፀው መጽሐፍ
Pinterest – እደ ጥበቦች፣ መዝሙሮች እና እንቅስቃሴዎች በ Sifriyat Pijama በ Pinterest ገጽ ውስጥ።
ስለ እጅ የሚገልፀው መጽሐፍ
ማንበብ፣ መዘመር እና መንቀሳቀስ
ታዳጊው የሚደጋገመውን ዓረፍተ ነገር ያጠናቅቀው፦ “ወዴት፣ ወዴት? ወደ መዋዕለ ህፃናት!”
እንቅስቃሴዎችን መጨመር፣ ማጨብጨብ ወይም የሙዚቃ መሳሪያዎችን መጠቀም ይችላሉ።
ወዴት? ወደ መዋዕለ ህፃናት!
የጠዋት ስነ-ስርአታችን
ተደጋጋሚ የጠዋት ድርጊቶች ታዳጊዎች ቀኑን በጥሩ ሁኔታ እንዲጀምሩ ይረዳቸዋል፦
ልብሱን አብሮ ማዘጋጀት፣ አስደሳች መዝሙር መዘመር፣ በመንገድ ላይ ቅጠሎችን ወይም ቀንበጦችን መሰብሰብ፣ ወይም ቋሚ በሆነ የሚያበረታታ ሰላምታ ቻዎ ማለት።
ወዴት? ወደ መዋዕለ ህፃናት!
ስዕላዊ ማብራሪያዎች ተረትን ይናገራሉ
አንድ ላይ ይመልከቱና ታዳጊው እንዲያገኝ ያድርጉ፦ ወፏ የት አለች? በተጨማሪ ገጾች ላይ ነውን? ልጁን ወደ መዋዕለ ህፃናት የሚሸኘው ማነው? ወደ መዋዕለ ህፃናት እንዴት እንሄዳለን – በብስክሌት፣ በእግር ወይም በሌላ መንገድ? ኮፍያ የሚለብሰው ማን ነው እና ውሻው የት አለ?
የመጨረሻውን ገጽ ይመልከቱ እና ይጠይቁ፦ “በመዋዕለ ሕፃናት ውስጥ ያሉ ልጆች ምን እያደረጉ ነው? በመዋዕለ ሕፃናት ውስጥ ምን ማድረግ ትወዳለህ/ትወጃለሽ?
ወዴት? ወደ መዋዕለ ህፃናት!
ጨዋታ፦ ወዴት?
ይጠይቁ፦ ወዴት፣ ወዴት? እና በእያንዳንዱ ጊዜ የተለየ ቦታ ይምረጡ፦ ወደ… መታጠቢያው፣ በረንዳው ወይም ወደ… የመጫወቻ ስፍራው? ወደ መረጡት ቦታ አብራችሁ ሂዱ፣ እርስ በርሳችሁ ተቃቀፉ እና ከዚያም ጮክ ብላችሁ ተናገሩ፦ ወዴት? ወዴት? ወደ… የሚቀጥለው ቦታ!
ወዴት? ወደ መዋዕለ ህፃናት!
ወዴት? ወደ መዋዕለ ህፃናት!
ውይይት - በምናብ አብሮ ማሰብ
ወንድና ሴት ልጆች የምናብ ጨዋታዎችን መጫወት ይወዳሉ። አዋቂ መስሎ መኪና ለ”መንዳት” መሞከር፣ ከጭቃ “ኬክ” መስራትና ከምናባዊ ጓደኛቸው ጋር መጫወት ያስደስታቸዋል። እንደ አሻንጉሊት፣ ድስት ወይም የመጫዎቻ መኪና ባሉ ነገሮች ዙሪያ ከልጆች ጋር አብሮ መጫወትና መጠየቅ ይቻላል – ወደየት እየሄድን ነው? አብረን ምን እናብስል? አሻንጉሊቱ ምን ይላል?
ምስል
ፈጠራ - በውሃ ውስጥ ያለ ነጸብራቅ
ነጸብራቅ መስራት ይፈልጋሉ? በኩሬው ውስጥ እንደሚያዩት? – የኪው አር ኮዱን ስካን በማድረግ ለቀላል ፈጠራ መነሳሻን ማግኘት ይችላሉ።
ምስል
ጨዋታ - ራሱን ቁጭ
ሮን በኩሬው ውስጥ አንድ ምስል ተመለከተ፤ ነገር ግን በእውነቱ በውሃው ውስጥ የሚንፀባረቀው የራሱ ምስል ነው። የ”መስታወት” ጨዋታን መጫወት ይችላሉ። ሁለት የቤተሰብ አባላት እርስ በእርሳቸው ፊት ለፊት ይቆማሉ፦ በተራው መሰረት አንዱ “የፊት ቅርጽ” እየሰራ ጭንቅላቱን ወይም እግሩን ያንቀሳቅሳል፤ ሌላኛው ደግሞ እርሱን ለመምሰል ይሞክራል።
ምስል
እንቅስቃሴ - በኩሬ ውስጥ መዝለል
ከውጪ በኩል ኩሬዎች አሉ? – ቡትስ ጫማዎችን በማድረግ በደንብ ለብሶ ወደ ውጪ መውጣትና በኩሬ ውስጥ መዝለል ይችላሉ። መውጣት ተገቢ ካልሆነስ? – ከገመድ ወይም ከወረቀት “ኩሬ” መስራትና የፈለጉትን ያህል ወደ ውስጥና ወደ ውጪ መዝለል ይችላሉ…
ምስል
פינטרסט
עוד יצירות והשראה מחכים לכם בתיקיית הספר בפינטרסט של ספריית פיג’מה!
ምስል