እንኳን ደህና መጣችሁ ውድ ወላጆች!
16/07/2023 | 277 צפיות
ብዙዎቻች በሕጻንነታችን የተነገሩንን ጥንታዊ ትረካዎችና ታሪኮችን እንወዳለን ፤ ከዓመታት በውኅላ እነዚህ ታሪኮች ከልባችን ውስጥ ይጠበቃሉ፤ ምክንያቱም ሞቅ ያለ ትዝታን በመያዝ በመኝታ ጊዜዎቻችን አልጋችን አጠገብ ሆነው በማቀፍ ተወዳጁን የትልቆችን የንባብ ድምፅ ስንሰማ ስለነበር ነው።
እኛ በመኝታ ሰዓት የሚነበቡ መጽሃፎች ወይም በስፍሪያት ፕጃማ (Sifriyat Pijama) የሕጻናትን መጽሐፎች ጠቃሚነት እንገነዘባለን፤ ምክንያቱም የቋንቋ ችሎታ መዳበርን፤ የብልህነት ስሜትን የሚያሳድግ ፤ መተዛዘንንና የማስተዋል አመለካከትን ፤ እንዲሁም የቤተሰብን የጊዜ አጠባበቅ ሁሉ ስለሚረዳ ነው። የእረጅም ጊዜ የማንበብ ፍቅርን ስለሚያበረታታ፤ እንዲሁም በቤተሰብ ዙሪያ የውይይት ባሕልን (ስርዓቶችን) በማሳደግ የይሁዲን እሴቶች (ዋጋ ያላቸውን ባሕላዊ ቅርሶች) የእስራኤላዊነት ውርስም ይጠብቃል። ፕሮግራሙ 8 ስዕላዊ መጽሐፎችን ለክፍሉ ልጆች ያዳርሳል ። እነዚህ መጸሕፍት ለእናንተ እንደስጦታ ሆነው ቤተሰቡ በአንድነት ይደሰትባቸዋል።
ነገር ግን መጸሐፍቹ በእብራይስጥ ቋንቋ የ ተጻፉ ናቸው !
ከዚህ በመቀጠል ያሉት ምክሮች በመኝታ ሰዓት የሚነበቡ መጽሃፎች ወይም በስፍሪያት ፕጃማ መጸሕፍትን ከልጆቻችሁ ጋር እንዴት እንደምትደሰቱባቸው የሚቁሙ ናቸው ፦
የእብራይስጥ ቋንቋ የችሎታችሁ ደረጃ ገና ብቃት ከሌለው ፣ልጆችሁ መጸሐፍቱን እንዲያነቡላችሁ ጋብዙት/ጠይቁት ። ልጃችሁ ይህን ታሪክ በመዋለ ህጻናት ወይም በትምህርት ቤት ተነግሮት የሚያውቀው ስለሆነ ፤ለእርሱ ቀላል ነው፤ እሱን/እርሷን ጠይቁና ስዕሎችን እንዲያሷያችሁና እንዲያነቡላችሁ አድርጉ ። እንዲያውም አንዳንድ አዳዲስ የእብራይስጥ ቃላትንም ከልጆቻችሁ ትማራላችሁ ።
በእያንዳንዱ መጽሐፍ ጀርባ ያሉት ሃሳቦች ቤተሰቡ በታሪኮች ዙሪያ እየተደሰተና እየተቀላለደ ይስማቸዋል ። በትውልድ ቋንቋችሁ እንዲተረክ መሆን አለበት፣
ንድ ድርጊትን ወይም የሐሳብ ውይይትን ምረጥና ከልጆቻችሁ ጋር በአንድነት ተደሰት፣
የቤተሰብህን ጓደኛ ጠይቅና ፤ ትላልቆች ልጆች ወይም ጎረቤት ጋር በእብራይስጥ ቋንቋ የተጻፈውን መጽሐፍ ከልጆችህ ጋር አንብቡት፤ ከመጀመሪያ ንባባችሁ በኋላ አንተም ድምጽህን ከፍ በማድረግ የማንበብ ልምምድ አድርግና በእብራይስጥ ቋንቋ በልጆችህ ፊት ማንበብ መተማመንን ይሰጥሃል።
በመኝታ ሰዓት የሚነበቡ መጽሃፎች ወይም በስፍሪያት ፕጃማ መጻሕፍትን እንደ ማዘለያ እስፕሪንግ አድርጋችሁ በመጠቀም የህጻንነት ትዝታዎቻችሁን ከልጆቻሁ ጋር በመጨዋወትና ለእነርሱም ተመሳሳዩን ታሪክ ለማስታውስ በትውልድ ቋንቋችሁ ተጠቀሙ።
በመኝታ ሰዓት የሚነበቡ መጽሃፎች ወይም በስፍሪያት ፕጃማ በመጠቀም እንዲደሰቱ ፣ለሌሎች አዲስ ገቢዎች የምታቀርቡት አስተያየት አላችሁን ? ካለ እንድንሰማው እንፈልጋለን ! ከእኛ ጋር በቀላሉ ለመገናኘትም ትችላላችሁ። pjisrael@hgf.org.il.
ለእናንተና ለልጆቻቹ አስደሳች ንባብ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን !